ወሳኙ መገለጥ

ትምህርተ ክርስቶስ

Mamusha Fenta

Stream the sermon 

ወሳኙ መገለጥ

ትምህርተ ክርስቶስ

Mamusha Fenta

ወሳኙ መገለጥ

  • 📖 ማቴ 16:13-20

በዚህ ትምህርት ሰውነቱንና አምላክነቱን ሁለቱን እንዴት አጣምሮ እንደያዘ ስራውንም እንመለከታለን። የክርስቶስ መገለጥ ወሳኝ መገለጥ ነው።

1) የኢየሱስ ማእከላዊነት (THE CENTRALITY OF CHRIST)

  • ክርስትና ብዙ የሚታይ ነገር አለው ፤ ነገር ግን ትኩረት ኢየሱስ ላይ ሲሆን ወደ ፍጻሜ ያደርሳል፣ ያበረታል።
  • የመሸነፍ ምክንያት ሁሉን ለማየት መሞከር ነው።
  • የኑሮ መሠረት ትኩረት ኢየሱስ ላይ።
    • 📖 ዕብ 12:1-2
  • የምንቃኘው ነገር ቢኖርም ትኩረት ግን ኢየሱስ ላይ ብቻ።
  • የእምነት አባቶች ቢኖሩም ምሳሌነታቸውን እዩ፣ ቃኙ ግን ትኩረት ኢየሱስ ላይ ብቻ።
  • ለመኖር፣ ለመጨከን፣ ለመጨረስ ትኩረት ኢየሱስ ላይ ብቻ።

📌 ለምን ትኩረት በኢየሱስ ላይ ብቻ?

1) ኢየሱስ ክርስቶስ የወንጌል ማዕከል ስለሆነ

  • ወንጌል ብዙ ሰዎች አሉበት፣ ብዙ ርዕሰ ጉዳዮች አሉበት ዋና ትኩረቱ ግን ኢየሱስ ብቻ ነው።
  • ሌሎቹ ወደ ኢየሱስ ጠቋሚ/ አመላካች/ ምስክር ናቸው።
  • ኢየሱስ የወንጌል ዋና ገጸ ባህሪ ነው።
  • ወንጌል እግዚአብሔር እንጂ ከብዙ ርዕሶች አንዱ አይደለም።
  • ወንጌል ብስራት፣ የምስራች ነው። የምስራች ሁሉ ግን ወንጌል አይደለም፤ መልካም ነገር ሁሉ ግን ወንጌል አይደለም።
    • 📖 ሮሜ 1:1-4
  • የእግዚአብሔር ወንጌል ስለልጁ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ኢየሱስ ሰው ነው – ከዳዊት ዘር፣ አምላክ ነው – የእግዚአብሔር ልጅ።
  • ክርስቶስን ትንሣኤው የእግዚአብሔር ልጅ አላደረገውም፤ በኃይል ገለጠው እንጂ።
  • የፈለግነውን እያወራን ወንጌል ነው ማለት አንችልም። የወንጌል ማዕከል ኢየሱስ ብቻ ነው፤ አይሻሻልም ደግሞም አይለወጥም።
    • 📖 1ቆሮ 15:1-4

2) እግዚአብሔርን ማወቂያ ብቸኛ መንገድ እሱ ስለሆነ

  • ወደ እግዚአብሔር መድረሻ መንገድ ኢየሱስ ብቻ ነው።
  • ኳስ በሌለበት ጨዋታ እንደሌለ ኢየሱስ በሌለበት እግዚአብሔር የለም።
  • ኢየሱስን ያጣ ሁሉን አጣ።
  • መንገደኞች ሁሉ ወደ ኢየሱስ አያደርሱም። ወደ እግዚአብሔር መድረሻ ብቸኛው መንገድ ኢየሱስ ብቻ ነው።
  • ኢየሱስ መንገዱም ሕይወትም እሱ ነው፤ ሌላ መንገድ የለም።
    • 📖 ዮሐ 1:18
    • 📖 ሐዋ ሥራ 4: (መዳን በማንም የለም) በሩ ኢየሱስ ነው።

3) የእግዚአብሔር ኃይል/ሥራ መገለጫው መንገድ እሱ ስለሆነ

  • እግዚአብሔር ምንም ነገር የሚሠራው በክርስቶስ ነው።
  • የእግዚአብሔር ኃይል የተገለጠበት አንዱ የፍጥረት ሥራ ነው። በሰማይና በምድር ያሉትን ሁሉ እንዴት ፈጠረው? በክርስቶስ!
    • 📖 ቆላ 1:15-17
  • ፍጥረት የተጋጠመው በኢየሱስ ነው።
    • 📖 ዕብ 1:1-3
  • ቀድሞም አሁንም የእግዚአብሔር ኃይል የተገለጠው በክርስቶስ ነው።
  • የሰውና የእግዚአብሔር መካከለኛ ኢየሱስ ነው።
  • መዳን መገለጫው ኢየሱስ ነው።
    • 📖 1ጢሞ 2:5
    • 📖 ሐዋ ሥራ 4:12
  • የእግዚአብሔር ኃይ በክርስቶስ ሲገለጥ እናያለን።
    • 📖 ኤፌ 1:9-10
  • አለም በክርስቶስ ትጠቀለላለች፤ ገዢው ኢየሱስ ነውና።
  • የሕይወት ቁልፉ አንድ ነው እሱም ኢየሱስ ብቻ።
  • ክርሰቶስን እግዚአብሔር እንደተረከው ብቻ ነው ማወቅ ያለብን።

Share:

Recommended...

1ኛ ቆሮንቶስ ትምህርት 12

Meskelun Menor by Mamusha Fenta on 1 Corinthians – Chapter 5 – Part 2 “መስቀሉን መኖር” 1ኛ ቆሮንቶስ : ምዕራፍ 5 – ክፍል 2 በማሙሻ ፈንታ

...
Mamusha Fenta

ትምህርተ ቤተ ክርስቲያን

No data was found

የቆላስይስ ትምህርት 24

The Supremacy Of Christ (colossians) Part 23 A by Mamusha Fenta

...
Mamusha Fenta

Order Spiritual Maturity | A Book by Mamusha Fenta


Pickup location: Lighthouse Cafe, ACLA Church, Addis Ababa, Ethiopia

Filter by Preacher

Filter by Topic

Filter by Scripture

Filter by Resource Type

Resource Type

Filter by Series

Series