መንፈስ ቅዱስ ማን ነው

ትምህርተ መንፈስ ቅዱስ

Mamusha Fenta

Stream the sermon 

መንፈስ ቅዱስ ማን ነው

ትምህርተ መንፈስ ቅዱስ

Mamusha Fenta

ትምህርተ መንፈስ ቅዱስ (DOCTRINE OF HOLY SPIRIT) ኒውማቶሎጂ

መንፈስ ቅዱስ ማን ነው?

THE IDENTITY OF HOLY SPIRIT

📌 ማንነቱን እንመለከታለን

  • 📖 ዮሐ 14:15-18

● ጥቂት የመንደርደሪያ አሳቦች

  • አንዳንዶች መንፈስ ቅዱስን “የተዘነጋው አምላክ” ይሉታል። ስለ ክርስቶስና ስለአብ ቡዙ ይባላል፤ ስለ መንፈስ ቅዱስ ግን ብዙም አይነገርም።

► ትምህርተ መንፈስ ቅዱስን ለምንድነው የምንማረው?

1) የእግዚአብሔርን ሥራ የምንለማመደው በመንፈስ ቅዱስ ስለሆነ

  • እግዚአብሔር የሚሠራውን አስፈጻሚ አካል መንፈስ ቅዱስ ነው።
  • በስላሴ አካል ውስጥ የተግባር ልዩነት እንዳለ ቀደም ባሉት ክፍሎች ተምረናል። የአብን ፍቅር፣ የወልድን መስእዋትነት በሕይወታችን የተለማመድነው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነው።
  • መንፈስ ቅዱስን ማወቅ ማለት እግዚአብሔርን ማወቅ ማለት ነው።
  • የእግዚአብሔር ሥራ በሕይወታችን የምንለማመደው ነው፤ የምናሠላስለው ወይ በሩቅ የምናየው አይደለም። የእግዚአብሔርን ፍቅሩን፣ ማዳኑን፣ ኃይሉን የምንለማመደው በመንፈስ ቅዱስ ነው።
  • መንፈስ ቅዱስን አለማወቅ የእግዚአብሔርን ሥራ አለማወቅ ነው፣ መንፈስ ቅዱስን ከማወቅ መጉደል ከእግዚአብሔር ሥራ መጉደል ነው።
  • መንፈስ ቅዱስን ያወጣ የክርስትና ሕይወት ባዶ ነው። ድነትን በሕይወታችን ሥጋ ያለበሰው መንፈስ ቅዱስ ነው።

2) በመንፈስ ቅዱስ ዙሪያ መጥራት ያለበት ትርምስ ስላለ

  • የመንፈስ ቅዱስ ልምምድ ወይም በመንፈስ ቅዱስ ዙሪያ ያለ ማንኛውም ልምምድ የሚፈተሽ ነው፤ አይነኬ አይደለም።
  • የመንፈስ ቅዱስ ልምምድ ከእግዚአብሔር መሆኑን የምናውቀው ለመነካት ክፍት ሲሆን ነው። ለምሳሌ ትንቢት (1ኛ ቆሮ 14: —ተራ በተራ ይናገሩ) የእግዚአብሔር ነገር ስርአት አለው። ይመዘናል፣ ይፈተሻል።
  • ለመመዘን ክፍት ያልሆነ፣ ፈቃደኛ ያልሆነ ነገር ሁሉ ከእግዚአብሔር ሊሆን አይችልም።
  • የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በሕይወታችን የእውነት እንዲገለጥ የመንፈስ ቅዱስን ትምህርት መማር አለብን። ሳይማሩ፣ ሲያውቁ የሚለማመዱ ሁልጊዜ ያበላሻሉ።
  • እግዚአብሔር ሥራው ስለማይቆም እኛ እንዲጠቀምብን ፈቃደኛ ብንሆን ጥሩ ነው።
  • ባወቅን ቁጥር የራሳችን መለኪያና መፈተሻ፣ መመዘኛና መመርመሪያ ይኖረናል።

📌 እንዴት እንማር ?

1) በሚጠማ ልብ

  • እግዚአብሔር የተጠሙትን ያጠጣል፤ ለመለማመድ፣ ለመጨበጥ እየተጠማን እንማር።
    • 📖 1ተሰ 5:19
  • ለመመራመር ሳይሆን ለመያዝ እየተጠማን እንማር።
  • በመረጃ ብቻ ሳይሆን ለመለማመድ መጠማት።
  • በዚህ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ስም የመንፈስ ቅዱስ ነገር ተዝረክርኳል። በዚህ ምክንያት ብዙዎች በቃኝ ብለው ጥግ እንዲቀመጡ ሆነዋል። ነገር ስቷል ማለት ግን እውነተኛው የለም ማለት አይደለም። የእውነት መንፈስ ቅዱስ አለ።
  • ራስን የመቻል መንፈስ አንዱ የመጠማት እንቅፋት ነው። ሁሉ አለኝና በራሴ እወጣለሁ የሚል አስተሳሰብ። መንፈስ ቅዱስ ያለአንተ አንችልም የሚለው ነገር የተወሰደበት።

2) በሰፊ ልብ

  • ሁሉ አይገባንም፣ ሁሉን አናውቅም፣ ልዩነቶች አሉን፤ መንፈስ ቅዱስን በተመለከተ የዳንን ክርስቲያኖች ልዩነቶች አሉን። ነገር ግን አብረን እንጸልያለን፣ እንማራለን። በመንፈስ ቅዱስ ማንነት ላይ አማኞች ልዩነት የለንም፣ ሥራው ምንድነው፣ ሥራው በፍጥረት ላይ፣ በአማኞች ላይ የሚሠራው ምንድነው፤ ልዩነት አለ። ልባችንን ሰፋ አድርገን ሌሎችን እኔ ከማምነው ውጪ የሚያምኑ ወገኖቼ የሚያምኑትን ፌር ሆነን ልንናገር ይገባል፤ ባንሠብከውም፣ ለማሳመን ባንጥርም፣ ግን በሰፊ ልብ እንናገር። የምናምነውን፣ አቋማችንን ግን አለመስበክ አይቻልም።
  • Respecting one another!
  • በመንፈስ ቅዱስ አማኞች ትዕቢት፣ ሌላውን መናቅ አለ። በልሳን የማይጸልይ፣ የማይጮህና የማይዘል መንፈስ ቅዱስ እንደሌላ እናስባለን። መንፈስ ቅዱስ የመኖሩ መለኪያ ግን የኛ ስሜት አይደለም።

3) በደፋር ልብ

  • እውነቱን የሚናገር፣ ስለ ልምምድ ብሎ እውቀትን የማይንድ።
  • ሆደ ሰፊነት የእግዚአብሔር ክብር እስከተጠበቀ ድረስ ብቻ ነው።
  • በትንቢት፣ በፈውስ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሁሉን እንቀበል አይደለም። ስህተትን ስህተት የሚል።
    • 📖 1ዮሐ 4:1
  • ቅዱስ ቃሉን የጣለ ልምምድ ከመንፈስ ቅዱስ አይደለም።
  • በመንፈስ ቅዱስ ስም የሚመጣ ግሳንግስ ብዙ ነው።

📌 ማነነቱ

1) የመንፈስ ቅዱስ አካላዊነት (PERSONHOOD)

  • አካል አለው ስንል BODY ማለታችን አይደለም። የራሱ ማንነት ያለው ማለት ነው።
  • መንፈስ ቅዱስ እርሱ ‘HE’ ነው ‘IT’ አይደለም።
  • መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስን ለመግለጥ የተጠቀመባቸው ሁለት ቃላት አሉ፥
    • ሩአኽ (ዕብ) – በብሉይ ኪዳን
    • ኒውማ (ግክ) – በአዲስ ኪዳን
  • ሁለቱም ትርጉማቸው ነፋስ/ ትንፋሽ/ እስትንፋስ ማለት ነው።
  • መንፈስ ኃይል ብቻ የሚመስላቸው አሉ። (ያኽዌ ምስክሮች)። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ኃይል አለው እንጂ ኃይል ብቻ አይደለም፤ አካል አለው።
  • አንድ ነገር አካላዊ ነው ለመባል 3 ነገሮች ያስፈልጉታል። መንፈስ ቅዱስም አሉት።

1) እውቀት :- ያውቃል፣ ይመረምራል

  • 📖 1ቆሮ 2:10-11

2) ስሜት:- ያዝናል፣ ይደሰታል፣

  • 📖 ኤፌ 4:30
  • 📖 ኢሳ 63:9-10

3) ፈቃድ :- እንደሚፈቅድ፣ እንደወደደ ያደርጋል፣ ይመርጣል፣ ይለያል

  • 📖 1ቆሮ 2:11
  • 📖 ዮሐ 3:8
  • 📖 ሐዋ 13:2
  • ለሉአላዊነቱ መስገድ ይጠበቅብናል።

2) አካላዊ ተግባራት አሉት

  • 📖 ዮሐ 14-16
  • ያስተምራል (ዮሐ 14:26)
  • ይመሰክራል (ዩሐ 15:26)
  • ይመራል (ዮሐ 16:13)
  • ይጠራል (ሐዋ 13:2)
  • ይጸልያል (ሮሜ 8:26)

3) አካላዊ መገለጫዎች አሉት

  • አጽናኝ (ጰራቅሊጦስ) PARACLETE ፓራካሊተስ / ፓራካሌኦ
  • ► ፓራ- አጠገብ —– ካሌኮ- መጠራት
  • አጠገብ ለመሆን ተጠርቶ የቆመ ማለት ነው።
    • 📖 ዮሐ 15:26
    • 📖 ሐዋ 15:29

Share:

Recommended...

የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት 67

ማቴዎስ ወንጌል 13:53-58 (አማ54) ኢየሱስም እነዚህም ምሳሌዎች ከጨረሰ በኋላ ከዚያ ሄደ።ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በምኩራባቸው ያስተምራቸው ነበር፤ እንዲህም አሉ። ይህን ጥበብና ተአምራት ይህ ከወዴት አገኘው?ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን? እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት...

Nigussie Bulcha

1ኛ ቆሮንቶስ ትምህርት 7

Meskelun Menor by Mamusha Fenta on 1 Corinthians – Chapter 3 – Part 1 “መስቀሉን መኖር” 1ኛ ቆሮንቶስ : ምዕራፍ 3 – ክፍል 1 በማሙሻ ፈንታ

...
Mamusha Fenta

ኤፌሶን ትምህርት 38

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:15–20 (አማ54) እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ። መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤ በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና...

Mamusha Fenta

Order Spiritual Maturity | A Book by Mamusha Fenta


Pickup location: Lighthouse Cafe, ACLA Church, Addis Ababa, Ethiopia

Filter by Preacher

Filter by Topic

Filter by Scripture

Filter by Resource Type

Resource Type

Filter by Series

Series