ከአምና…ዘንድሮ

Mamusha Fenta

Stream the sermon 

ከአምና…ዘንድሮ

Mamusha Fenta
Scripture: Romans 13

ሩቅ መንገድ ለመሔድ ተነስተን ስንጀምረው የሚደረስ አይመስልም። በመንገዳችን ዳር የተተከሉ የርቀት አመልካቾችም በጉዟችን ጅማሬ ላይ የሚያሳዩን ባለ ሦስትና አራት አሀዝ የኪሎ ሜትር ወይም ማይል ቁጥር ቶሎ መድረስ ለሚፈልግ መንገደኛ አታካች ናቸው። 

አንድ ሐቅ ግን ግልጽ ነው። አንድ ኪሎ ሜትር በነዳን ቁጥር ከሚቀረን ረጅሙ ርቀት ወስጥ አንድ ተቀንሷል። በሌላ አገላለጽ፡- ቅድም ከነበርንበት ርቀት በአንድ ኪሎ ሜትር  ወደ ፍጻሜያችን ተጠግተናል። ወደፊት በሔድን ቁጥር መድረሻችን ቀርቧል ማለት ነው።

ብዙ ጊዜ ባናስተውለውም ዘመንም እንዲሁ ነው። አንድ ዘመን በተጨመረልን ቁጥር ወደ ፍጻሜያችን በአንድ ዘመን ቀርበናል ማለት ነው። ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን ትላንት፣ ዛሬ፣ አምና፣ ዘንድሮ እያልን ስንቆጥር ወደ መጨረሻዉ (ወደ መዳናችን) እየተጠጋን ነው:- “ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና” ይላል (ሮሜ 13፡11)።  ደግሞም “…የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል” (1ጴጥ 4፡7) ብሎ ያሳስበናል።

በርግጥ ይህ እውነት ተዘጋጅተው ለሚኖሩ የሚያናውጥ ወይም አስደንጋጭ ሊሆን አይገባም (2ተሰ 2፡12)። ነገር ግን በማቴ 25 ላይ እንደ ተጠቀሱት በደንብ እስከ መጨረሻ ያልተዘጋጁ አምስቱ ሙሽራ ጠባቂ ቆነጃጅት የማንቂያ ደወል ነው። እንቅልፍ እንቅልፍ ባለን ጊዜ ማሰብ ያለብን እውነት ከትላንት ይልቅ ዛሬ እየተጠጋን መሆናችንን ነው። የማንቀላፋትና የለዘብተኝነት ዘመን አይደለም።

በአገራችን ዘመን አቆጣጠር አዲስ አመት ልንቀበል ነው። ነገ ‘ዘንድሮ’ ይሆንና ዛሬ ደግሞ ‘አምና’ ይባላል። የሕይወት ዘመን መቁጠሪያችን አንድ አመት ወደ ፍጻሜያችን መጠጋታችንን ታበስራለች። ቀን መቁጠሪያው በአንድ አመት በጨመረ ቁጥር መጨረሻው በአንድ አመት መቅረቡን መገንዘብ ለብዙዎቻችን አዳጋች አይመስለኝም። እንግዲያውስ አዲሱን አመት ስናከብር ከአምና ይልቅ ዘንድሮ ወደ ፍጻሜው መጠጋታችንን እያሰብን ይሁን። ስለሆነም በደስታ፣ በናፍቆትና በንቃት የበለጠ የምንዘጋጅበት ዘመን መለወጫ ይሁንልን።

ከአምና ይልቅ ዘንድሮ መዳናችን ቀርቧል- እንግዲህ እንንቃ!

መልካም አዲስ ዓመት!

Share:

Recommended...

ኤፌሶን ትምህርት 49

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6:5-9 (አማ54) ባሪያዎች ሆይ፥ ለክርስቶስ እንደምትታዘዙ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ በልባችሁ ቅንነት በሥጋ ጌቶቻችሁ ለሆኑ ታዘዙ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደሚያደርጉ እንደ ክርስቶስ ባሪያዎች እንጂ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ አትሁኑ። ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምትገዙ በትጋትና በበጎ ፈቃድ ተገዙ፤ ባሪያ ቢሆን ወይም ጨዋ ሰው፥ እያንዳንዱ የሚያደርገውን መልካም ነገር ሁሉ ከጌታ በብድራት...

Aberham Teklemariam

የዮሐንስ ወንጌል ትምህርት መግቢያ

“Hiwot Tegelete” Teaching on The Gospel of John, Introduction by Mamusha Fenta

...
Mamusha Fenta

ጰራቅሊጦስ 2016 ቀን 4

ጰራቅሊጦስ2016 መንፈስ ቅዱስ ሳምንት መንፈስ ቅዱስ እና የእግዚአብሔር ቃል : በአብርሃም ተ/ማርያም : By Abraham T/Mariyam

...
Aberham Teklemariam

Order Spiritual Maturity | A Book by Mamusha Fenta


Pickup location: Lighthouse Cafe, ACLA Church, Addis Ababa, Ethiopia

Filter by Preacher

Filter by Topic

Filter by Scripture

Filter by Resource Type

Resource Type

Filter by Series

Series