የጦር ሜዳ

Scripture: Matthew 24
Mamusha Fenta

Stream the sermon 

የጦር ሜዳ

Mamusha Fenta
Scripture: Matthew 24

በእኔ አመለካከት ትርጉማቸዉ በፍጥነት እየተቀየሩ ከመጡ ሃሳቦች መካከል አንዱ “የጦር ሜዳ” የሚለዉ ነው። ቃሉ ለዘመናት ያገለገለዉ ከሰላማዊ ሰዎች መኖሪያ ወጣ ተብሎ ለጦርነት የሚያገለግልን ሥፍራ ለማመልከት ነዉ። የጥንት ጦርነቶች ከከተማ ቅጥሮች ዉጪ ተካሂደዉ፤ ያሸነፈዉ አካል ለምርኮና ለብዝበዛ ወደ ከተሞች ዘልቆ ይገባ ስለነበር ጦርነቶቹ የሚካሄዱበት የተለየዉ ሥፍራ ነዉ “የጦር ሜዳ” የሚባለዉ። አጠቃላይ ትርጉሙንና ልምዱ ለማሳየት እንጂ ከዚህ በተለየ መልኩ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ዘግናኝ ጦርነቶችም በሰዉ ልጅ ታሪክ ዉስጥ ነበሩ። በአጠቃላይ ግን “ጦር ሜዳ የሚሄድ ዘማች” እና “በቤት የሚቀር/በሰላማዊ ቦታ የዘወትር ተግባሩን የሚያከናዉን ዜጋ” የተለያዩ ነበሩ።

አሁን እንዲህ ያለ ነገር መቅረቱን በግልጽ እናስተዉላለን። ዓለም በሞላ የጦር ሜዳ ሆናለች። ያለንበት ማንኛዉም ቦታ (የሥራ፣ የገበያ፣ የመዝናኛ  ወ.ዘ.ተ.) በቅጽበት ወደ ጦር ሜዳነት ሊቀየር ይችላል። በጥቂት ቀናት ልዩነት የዋሽንግተን የባህር ኃይል መሥሪያ ቤትና የአሁኑ የጎረቤታችን ናይሮቢ ዘግናኝ እልቂቶች ይህንን ያመለክቱናል። ሰዎች በጠዋት ተነስተዉ ወደ ሥራ፣ገበያ፣ መዝናኛ እንጂ ወደ “ጦር ሜዳ” መሄዳቸዉን አላስተዋሉም። በነገራችን ላይ፣ ሰሞኑን እየታየ ባለዉ “ፊልም መሳይ” የሰላማዉያን እልቂት የተሰማኝ ሃዘንና የጸሎት ሸክም በቃል ልገልጸዉ አልችልም።

ታዲያ እንዲህ ባለ ዘመን፧-

አንደኛ ስለእያንዳንዷ ቀን የሕይወት ስጦታ፤ የሕይወታችንን ባለቤት እንድናመሰግን ሊያደርገን ይገባል። ሕይወትን እንደዘበትና እንደሚገባን ነገር አንቁጠር። በጦር ሜዳ ዓለም የተሰጠን ልዩ ጸጋ በመሆኑ ማመስገን ይገባል።

በሌላ በኩል ደግሞ የጌታችን ኢየሱስን ቃል ሊያስታዉሰን ይገባል (ማቴ 24፡6-7)። ጦርና የጦር ወሬ የመምጣቱ አንድ አመልካች/አስታዋሽ/ ደወል በመሆኑ ነቅቶ መኖርና መጠበቅ ይገባል።  “አትደንግጡ” ያለንን ጌታ ታምነን በእምነት “በሞት ጥላ መካከል እንኳን ብሄድ፣ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም” እንላለን። በተጨማሪም ለዘብተኛ መንፈሳዊነትን፣ ማፈግፈግን፣ መንፈሳዊ እንቅልፍን አስወግደን በትጋት ከጌታ ጋር እለት እለት መራመድ ግድ ነዉ። We can not afford to be weak or to backslide!

በመጨረሻም ክርስቶስን በግል በማመንና በመከተል መዳን ያስፈልገናል። ጌታን ስናምን ሞት አያስፈራንም፤ ምክንያቱም ከሁለተኛዉ ሞት (ከገሃነም) የተረፍን በመሆኑ። “ሞት ሆይ መዉጊያህ የት አለ” (2ቆሮ 15፡54) በሚል የትንሣኤ እምነት እንመላለሳለን።

በአጠቃላይ የዛሬዉ ምክሬ ይህ ነዉ፡- ዓለም ሁሉ ጦር ሜዳ ሆኗልና እንግዲህ ንቁ!

Share:

Recommended...

የቆላስይስ ትምህርት 7

The Supremacy of Christ colossians Part 7 by Mamusha Fenta

...
Mamusha Fenta

ትምህርተ መፅሐፍ ቅዱስ ክፍል 2

የእግዚአብሔር ቃል ትክክለኛነት (እውነተኛነት) 📖 መዝ 119:41-48፣, 97-104፣ 129-136 🏷 ጥቂት አስረጂዎች:-መጽሐፍ ቅዱስ ሲጻፍ የተጻፉባቸው ረቂቆች፣ ከዚያ በኋላ ደግሞ በመጡ ብዙ ሺህ ቅጂዎች፥ (የመጀመሪያዎቹ ረቂቆች) አሉ፤ እነኚህ በሙሉ እግዚአብሔር አለባቸው። ትክክለኛ እግዚአብሔር ማለት የፈለገውን የሚሉ ናቸው።እግዚአብሔር ሰዎችን ተጠቅሟል፤ ሰዎች ሲጽፉ፣ ኮፒ ሲያደርጉ፣ ሲተረጉሙ እግዚአብሔር የፈለገውን ነው የሚሉት።ትክክለኛ ማለት ይህ ነው፤...

Mamusha Fenta

የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት 117

በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ጌቴሴማኒ ወደምትባል ስፍራ መጣ ደቀ መዛሙርቱንም። ወዲያ ሄጄ ስጸልይ ሳለ በዚህ ተቀመጡ አላቸው። ጴጥሮስንም ሁለቱንም የዘብዴዎስን ልጆች ወስዶ ሊያዝን ሊተክዝም ጀመር። ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቆዩ ከእኔም ጋር ትጉ አላቸው። ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ። አባቴ፥ ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ...

Mamusha Fenta

Order Spiritual Maturity | A Book by Mamusha Fenta


Pickup location: Lighthouse Cafe, ACLA Church, Addis Ababa, Ethiopia

Filter by Preacher

Filter by Topic

Filter by Scripture

Filter by Resource Type

Resource Type

Filter by Series

Series