ወሳኙ መገለጥ
- 📖 ማቴ 16:13-20
በዚህ ትምህርት ሰውነቱንና አምላክነቱን ሁለቱን እንዴት አጣምሮ እንደያዘ ስራውንም እንመለከታለን። የክርስቶስ መገለጥ ወሳኝ መገለጥ ነው።
1) የኢየሱስ ማእከላዊነት (THE CENTRALITY OF CHRIST)
- ክርስትና ብዙ የሚታይ ነገር አለው ፤ ነገር ግን ትኩረት ኢየሱስ ላይ ሲሆን ወደ ፍጻሜ ያደርሳል፣ ያበረታል።
- የመሸነፍ ምክንያት ሁሉን ለማየት መሞከር ነው።
- የኑሮ መሠረት ትኩረት ኢየሱስ ላይ።
- 📖 ዕብ 12:1-2
- የምንቃኘው ነገር ቢኖርም ትኩረት ግን ኢየሱስ ላይ ብቻ።
- የእምነት አባቶች ቢኖሩም ምሳሌነታቸውን እዩ፣ ቃኙ ግን ትኩረት ኢየሱስ ላይ ብቻ።
- ለመኖር፣ ለመጨከን፣ ለመጨረስ ትኩረት ኢየሱስ ላይ ብቻ።
📌 ለምን ትኩረት በኢየሱስ ላይ ብቻ?
1) ኢየሱስ ክርስቶስ የወንጌል ማዕከል ስለሆነ
- ወንጌል ብዙ ሰዎች አሉበት፣ ብዙ ርዕሰ ጉዳዮች አሉበት ዋና ትኩረቱ ግን ኢየሱስ ብቻ ነው።
- ሌሎቹ ወደ ኢየሱስ ጠቋሚ/ አመላካች/ ምስክር ናቸው።
- ኢየሱስ የወንጌል ዋና ገጸ ባህሪ ነው።
- ወንጌል እግዚአብሔር እንጂ ከብዙ ርዕሶች አንዱ አይደለም።
- ወንጌል ብስራት፣ የምስራች ነው። የምስራች ሁሉ ግን ወንጌል አይደለም፤ መልካም ነገር ሁሉ ግን ወንጌል አይደለም።
- 📖 ሮሜ 1:1-4
- የእግዚአብሔር ወንጌል ስለልጁ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ኢየሱስ ሰው ነው – ከዳዊት ዘር፣ አምላክ ነው – የእግዚአብሔር ልጅ።
- ክርስቶስን ትንሣኤው የእግዚአብሔር ልጅ አላደረገውም፤ በኃይል ገለጠው እንጂ።
- የፈለግነውን እያወራን ወንጌል ነው ማለት አንችልም። የወንጌል ማዕከል ኢየሱስ ብቻ ነው፤ አይሻሻልም ደግሞም አይለወጥም።
- 📖 1ቆሮ 15:1-4
2) እግዚአብሔርን ማወቂያ ብቸኛ መንገድ እሱ ስለሆነ
- ወደ እግዚአብሔር መድረሻ መንገድ ኢየሱስ ብቻ ነው።
- ኳስ በሌለበት ጨዋታ እንደሌለ ኢየሱስ በሌለበት እግዚአብሔር የለም።
- ኢየሱስን ያጣ ሁሉን አጣ።
- መንገደኞች ሁሉ ወደ ኢየሱስ አያደርሱም። ወደ እግዚአብሔር መድረሻ ብቸኛው መንገድ ኢየሱስ ብቻ ነው።
- ኢየሱስ መንገዱም ሕይወትም እሱ ነው፤ ሌላ መንገድ የለም።
- 📖 ዮሐ 1:18
- 📖 ሐዋ ሥራ 4: (መዳን በማንም የለም) በሩ ኢየሱስ ነው።
3) የእግዚአብሔር ኃይል/ሥራ መገለጫው መንገድ እሱ ስለሆነ
- እግዚአብሔር ምንም ነገር የሚሠራው በክርስቶስ ነው።
- የእግዚአብሔር ኃይል የተገለጠበት አንዱ የፍጥረት ሥራ ነው። በሰማይና በምድር ያሉትን ሁሉ እንዴት ፈጠረው? በክርስቶስ!
- 📖 ቆላ 1:15-17
- ፍጥረት የተጋጠመው በኢየሱስ ነው።
- 📖 ዕብ 1:1-3
- ቀድሞም አሁንም የእግዚአብሔር ኃይል የተገለጠው በክርስቶስ ነው።
- የሰውና የእግዚአብሔር መካከለኛ ኢየሱስ ነው።
- መዳን መገለጫው ኢየሱስ ነው።
- 📖 1ጢሞ 2:5
- 📖 ሐዋ ሥራ 4:12
- የእግዚአብሔር ኃይ በክርስቶስ ሲገለጥ እናያለን።
- 📖 ኤፌ 1:9-10
- አለም በክርስቶስ ትጠቀለላለች፤ ገዢው ኢየሱስ ነውና።
- የሕይወት ቁልፉ አንድ ነው እሱም ኢየሱስ ብቻ።
- ክርሰቶስን እግዚአብሔር እንደተረከው ብቻ ነው ማወቅ ያለብን።