ሲሄዱም ሳሉ እነሆ፥ ከጠባቆቹ አንዳንድ ወደ ከተማ መጥተው የሆነውን ሁሉ ለካህናት አለቆች አወሩ። ከሽማግሎች ጋርም ተሰብስበው ተማከሩና ለጭፍሮች ብዙ ገንዘብ ሰጥተዋቸው። እኛ ተኝተን ሳለን ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰረቁት በሉ። ይህም በገዢው ዘንድ የተሰማ እንደ ሆነ፥ እኛ እናስረዳዋለን እናንተም ያለ ሥጋት እንድትሆኑ እናደርጋለን አሉአቸው። እነርሱም ገንዘቡን ተቀብለው እንደ አስተማሩአቸው አደረጉ። ይህም ነገር በአይሁድ ዘንድ እስከ ዛሬ ድረስ ሲወራ ይኖራል።
While the women were on their way, some of the guards went into the city and reported to the chief priests everything that had happened. When the chief priests had met with the elders and devised a plan, they gave the soldiers a large sum of money, telling them, “You are to say, ‘His disciples came during the night and stole him away while we were asleep.’ If this report gets to the governor, we will satisfy him and keep you out of trouble.” So the soldiers took the money and did as they were instructed. And this story has been widely circulated among the Jews to this very day.