አምላካችን ማን ነዉ?

Mamusha Fenta

Stream the sermon 

አምላካችን ማን ነዉ?

Mamusha Fenta
Scripture: Colossians 1

“እረሱ (ክርስቶስ) የማይታየዉ አምላክ አምሳል ነዉ፤ ከፍጥረትም ሁሉ በፊት በኩር ነዉ፤ ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ በሰማይና በምድር ያሉ፣ የሚታዩና የማይታዩ፣ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኀይላት፣ ገዦች ቢሆኑ ወይም ባለሥልጣናት፣ ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። እርሱ ከሁሉ በፊት ነዉ፤ ሁሉ ነገር በአንድ ላይ ተያይዞ የጸናዉ በእርሱ ነዉ። እርሱ አካሉ የሆነችዉ የቤተክርስቲያን ራስ ነዉ፤ በሁሉ ነገር የበላይነት ይኖረዉ ዘንድ እርሱ የመጀመሪያ፣ ከሙታን መካከልም በኩር ነዉ።” (ቆላስያስ 1፡15-18)

እግዚአብሔር “ሕዝቤን ልቀቅ” ባለ ጊዜ ፈርኦን የተናገረዉ ሁልጊዜ ተገዳዳሪዎቻችን በህሊናችን የሚያቃጭሉት ጥያቄ ነዉ። ፈርኦን “ቃሉን እሰማ ዘንድ እስራኤልንስ እለቅቅ ዘንድ እግዚአብሔር ማን ነዉ?” ነበር ያለዉ (ዘጸ 5፡2)። ዛሬም “አምላክህ/ሽ  ማን ነዉ?” ለሚለን ቆላ 1 አስደናቂ እዉነታ ነዉ። አምላካችን ክርስቶስ ፍጥረተ ዓለሙን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ ብቻ ሳይሆን አሁንም ፍጥረት ሥርዐት ይዞ እንዲቀጥል ሁሉን በአንድ ላይ አያይዞ ያስቀጥለዋል፣ ያጸናዋል። ፍጥረት ምን እንደሚያክል፣ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ግዙፍ ከዋክብትና ክምችቶቻቸውም ምን እንደሚመስሉ ለማሰብ ያስቸግራል። እነኝህን ሁሉ በእጆቹ ይዞ የሚያጸናቸዉ… አምላካችን ነው (ኢሳ 40፡27-31)። ክርስቶስ የሁሉ ፈጣሪና የበላይ ነዉ። የኛ ችግርና ተግዳሮትማ ለእርሱ እንዴት ቀላል ነዉ? ስለሆነም  አማኝ ነፍሱን 

“እረፊ፣ አትጨነቂ፣ አትታወኪ፣ ዝም ብለሽ በኃያሉ አምላክሽ ታመኚ” ይበል፡፡

Share:

Recommended...

1ኛ ቆሮንቶስ ትምህርት 7

Meskelun Menor by Mamusha Fenta on 1 Corinthians – Chapter 3 – Part 1 “መስቀሉን መኖር” 1ኛ ቆሮንቶስ : ምዕራፍ 3 – ክፍል 1 በማሙሻ ፈንታ

...
Mamusha Fenta

የዮሐንስ ወንጌል ትምህርት 10

“Hiwot Tegelete” John Chapter 2: Part 3 by Mamusha Fenta

...
Mamusha Fenta

ኤፌሶን ትምህርት 42

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:22–33 (አማ54) ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና። ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ። ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ...

Mamusha Fenta

Order Spiritual Maturity | A Book by Mamusha Fenta


Pickup location: Lighthouse Cafe, ACLA Church, Addis Ababa, Ethiopia

Filter by Preacher

Filter by Topic

Filter by Scripture

Filter by Resource Type

Resource Type

Filter by Series

Series