መንገድ ላይ የቆመች መበለት ገፍቼ፣ “ምን ሆነሽ ነዉ?” ሳልል እንባዋን አይቼ፣ የጎዳናዉ ጩጬም “ስለእግዚአብሔር” ሲለኝ ፣ እርሱን ገላምጬ ጊዜ ስለሌለኝ፣ መስኮቴን ዘግቼ ጩዀቱን አርግቤ፣ ወደቤትህ ልደርስ ላመልክህ ከልቤ። ፍጥነቴን ጨምሬ ደጀሰላም ስደርስ፣ “ወድሃለሁ” የሚል የሕዝብህን ጩኸት ተደምሬ ሳደርስ፣ ደስ እንድትሰኝም ምስጋናዬን ሳጤስ፣ እጆቼን ዘርግቼ መስዋእቴን ሳፈሰዉ ምን እያልከኝ ይሆን በሰማይ...
Pickup location: Lighthouse Cafe, ACLA Church, Addis Ababa, Ethiopia