የማቴዎስ ወንጌል 11: 12-19 (አማ 54)
ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል። ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ፤ 14ልትቀበሉትስ ብትወዱ፥ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነው። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ። ነገር ግን ይህን ትውልድ በምን እመስለዋለሁ? በገበያ የሚቀመጡትን ልጆች ይመስላሉ፥ እነርሱም ባልንጀሮቻቸውን እየጠሩ፦ እንቢልታ ነፋንላችሁ ዘፈንም አልዘፈናችሁም ሙሾ አወጣንላችሁ ዋይ ዋይም አላላችሁም ይሉአቸዋል። ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፥ እነርሱም፦ ጋኔን አለበት አሉት። የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፥ እነርሱም፦ እነሆ፥ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ ይሉታል። ጥበብም በልጆችዋ ጸደቀች።
Matthew 11: 12-19 (ESV)
From the days of John the Baptist until now the kingdom of heaven has suffered violence, and the violent take it by force. For all the Prophets and the Law prophesied until John, and if you are willing to accept it, he is Elijah who is to come. He who has ears to hear, let him hear. “But to what shall I compare this generation? It is like children sitting in the marketplaces and calling to their playmates, “‘We played the flute for you, and you did not dance we sang a dirge, and you did not mourn.’ For John came neither eating nor drinking, and they say, ‘He has a demon.’ The Son of Man came eating and drinking, and they say, ‘Look at him! A glutton and a drunkard, a friend of tax collectors and sinners!’ Yet wisdom is justified by her deeds.”