እግዚአብሔርን ማወቅ

ትምህርተ እግዚአብሔር

Mamusha Fenta

Stream the sermon 

እግዚአብሔርን ማወቅ

ትምህርተ እግዚአብሔር

Mamusha Fenta
Scripture: Jude, New Testament

እግዚአብሔርን ማወቅ (Knowing God)

ይህ ትምህርት በስነ መለኮት አስተምህሮ Theology Proper ይባላል። ሌሎቹም ቲዎሎጂ ናቸው ይሔኛው ግን ዋና/ማዕከላዊ ነው። ምክንያቱም ሌሎቹን ቲዎሎጂ ብናጠና እግዚአብሔርን ለማወቅ ነው። እግዚአብሔርን ማወቅ የሰው ማዕከል ነው።

📍መግቢያ
📖 ት.ሆሴዕ 6:3-6

  • ስለ እግዚአብሔር የመማራችን አላማ እግዚአብሔርን ማወቅ ነው።
  • መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ህላዌ/መኖር በተመለከተ በክርክር አይጀምርም።
  • የኛ ዘመን ከመጽሐፍ ቅዱስ የራቀ ስለሆነ አምላክ የለም ብለው የሚያምኑ ሰዎች አሉ፤ ኤቲየስት ይባላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ሲጀምር “በመጀመሪያ እግዚአብሔር …” ብሎ እንጂ የሚጀምረው አለ ወይስ የለም? ብሎ አይደለም።
  • እግዚአብሔር ቢኖርም ማወቅ አይቻልም ብለውም የሚያምኑ አሉ አግኖስቲክስ ይባላሉ። መጽሐፍ እንደነዚህ ያሉ አስተሳሰቦችን የሞኝ አስተሳሰብ ነው። የሚለው።
    📖 ሮሜ 1:22 ላይ “ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ”
    📖 መዝ 14:1 “..ሞኝ/ሰነፍ በልቡ…”
  • እግዚአብሔር የለም ማለት የሞኝነት እንጂ የመራቀቅ ምልክት አይደለም።
  • አምላክ የለም የሚሉ ሰዎች ዋና የውስጥ ፍላጎት የፈለጉትን ለማድረግ ነው፣ ብልሹዎች ስለሆኑ ነው።
    📖 መዝ 10:3-4 “….ክፉ ሰው…”
  • ሰው “አምላክ የለም” የሚለው የለም በማለት እንደፈለገ መኖር ስለሚፈልግ ነው። የለም ማለት እንዳይኖር አያደርገውም፤ እግዚአብሔር አለ።
  • የተፈጥሮ ውበት የእግዚአብሔርን መኖር ገላጭ ነው።
  • የአለም ውበቷ፣ ከለሯ፣ የእያንዳንዱ ነገር አቀማመጥ፣ ተግባር ሁሉንም በልኩ የፈጠረ አምላክ አለ።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር መኖር በተመለከተ “አንድ እግዚአብሔር አለ፤ ማረጋገጥ ከፈለክ ሥራዎቹን ተመልከት” ይላል።

📍 እግዚአብሔርን የማወቅ አስፈላጊነት
እግዚአብሔርን ማወቅ ዋና ነገር ነው፣ የሰው ልጅ የመኖር ዋና አላማ እግዚአብሔርን ማወቅ ነው። እሱ ከሌለ አለም ይተራመሳል።
እግዚአብሔርን በማወቅ ያልረካች ነፍስ በምንም አትረካም።
በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠራችን እርሱን ለማወቃችን መንገዱ ነው።
📖 ት. ኤር 9:23-24
ሰው ሙሉ መሆን ከፈለገ እግዚአብሔርን ይወቅ።
ሌላ የማያስደግፍ ነገር ጥብቅ አድርጎ ከመያዝ የሚያስመካውን እግዚአብሔር መያዝ ይበልጣል።
🖊 ፍጥረት (Creation)
እግዚአብሔር አለማትን የፈጠረው ክብሩን ገልጦ እንድናውቀው ነው።
ፍጥረተ አለሙ ደግሞ በእግዚአብሔር በልኩ ነው የተፈጠረው።
📖 ሮሜ 1:20-21
እግዚአብሔር ክብሩን በፍጥረታት ውስጥ አድርጎ ፈጠረ ምክንያቱም እግዚአብሔርን እንዲያውቁትና በእግዚአብሔርነቱ እንዲያከብሩት።
የሰው ሞኝነቱ ፍጥረትን አይቶ ፈጣሪውን ትቶ ተፈጣሪውን ማማለኩ ነው።
🖊 ድነት (Salvation)
እንድናውቀው ነው ያዳነን። ገሃነምን ፈርተን ሳይሆን እንድናመልከው፣ እንድናውቀውና የራሱ ሊያደርገን ጭምር ነው ያዳነን።
መዳንና እግዚአብሔርን ማወቅ አንድ ናቸው (ገላ 4:8-9)።
📖 ዮሐ 17:3 …የዘላለም ሕይወት ናት…
ኃይማኖተኛ ሆኖ እግዚአብሔርን አለማወቅ ይቻላል።
📖 1ኛ ዮሐ 5:20-21
የእግዚአብሔር ልጅ የመጣው እግዚአብሔርን እንድናውቅ ነው።
🖊 መግቦት (Providence)
እግዚአብሔር ፍጥረቱን ሲመግብ፣ ሲንከባከብ አላማው እርሱን እንድናውቅ ነው።
እግዚአብሔር የሚሠራውን ሥራ ሁሉ የሚሠራው እንድናውቀው ነው።
በምናልፍበት መንገድ ሁሉ እግዚአብሔርን እንወቅ እንጂ ነገር ሁሉ ለመልካም ይሆናል።
፨ ሰው እግዚአብሔርን ሲያውቅ ለእግዚአብሔር ይኖራል፤ እግዚአብሔርን ሳያውቅ በኢሞራሊቲ ይሞላል።
እግዚአብሔር ሲፈጥርም፣ ሲያድንም፣ ሲመግብም እርሱን እንድናውቀው ነው።

📍 እግዚአብሔርን ማወቅ በተመለከተ ልናውቃቸው የሚገቡ ሦስት እውነቶችን እንመልከት።
1️⃣ የእግዚአብሔር ምጡቅነት
የእግዚአብሔር አይነኬነቱን በማወቅ እንጀምር።
እግዚአብሔርን እናውቀዋለን ግን ሙሉ በሙሉ አይደለም። ምክንያቱም እሱ ምጡቅ ነው፣ አይወሰንም፣ አይጨረስም።
“ምጡቅ”:- የመጠቀ፣ ከምድር የራቀ፣ ከፍተኛ፣ ረጅም፣ ሩቅ፣ ረቂቅ ማለት ነው (ከአለቃ ኪዳነ ወ/ክፍሌ መዝገበ ቃላት የተወሰደ)
እግዚአብሔርም እንደዚህ ነው፤ ስለ እግዚአብሔር ሁሉን አናውቅም፤ እውቀትን እንጂ።
እንኳን እግዚአብሔርን የፈጠረውንም አውቀን አልጨረስንም።
📖 ኢዮ 11:7
📖 መዝ 145:3
📖 መዝ 147:5
አለመታወቁ የአምልኳችን እንጂ የንጭንጫችን ምክንያት አይደለም።
📖 መዝ 139:17
📖 ኢሳ 55:9
የእግዚአብሔር ምጡቅነት ተስፋ አስቆራጭ ነገር አይደለም፤ እግዚአብሔር የበላይመሆኑ፣ ከፍ ያለ መሆኑ፣ ሀሳቡ የበላይ መሆኑ፣ የማይደረስበት መሆኑ ተስፋ አስቆራጭ ኮርስ አያደርገውም። የአምልኳችንና የጥማታችን ምክንያት ነው።
እውነተኛ ክርስቲያኖች ደረስኩበት አይሉም፤ እሱን በማወቅ ይቀጥላሉ።
📖 ሮሜ 11:33
📖 ቆላ 1:10
እግዚአብሔር በሰማይም አውቀን አንጨርሰውም። ሰማይ በአምልኮ የተሞላው አምልከን ልንጨርሰው በማንችለው አምላክ ፊት ስለምንኖር ነው።
2️⃣ የእግዚአብሔር ቅሩብነት
“ቅሩብ”:- የቀረበ፣ ቅርብ፣ አጠገብ፣ ዘመድ ተብሎ ተተርጉሟል (ከአለቃ ኪዳነ ወ/ክፍሌ መዝገበ ቃላት የተወሰደ)።
እግዚአብሔር ቅርብ ነው፣ የሚታወቅ ነው።
📖 ሐዋ ሥራ 14:15-17
እግዚአብሔር በጣም ምጡቅም ቅርብም ነው።
📖 ሐዋ ሥራ 17:26-28
📖 ሆሴዕ 6:3
እግዚአብሔር ከቅርበቱ የተነሳ ከሱ ጋር የግል ኀብረት ሊኖረን ይችላል።
አማኞች የእግዚአብሔርን ምጡቅነትና ቅርብነት አንድ ላይ ነው የምንይዘው።
🖊 Deism :- ምጡቅነቱን ለጥጦ የያዘ ፍልስፍና ነው፣ እግዚአብሔርን ከፍጥረተ አለም የሚያርቅ፣ እግዚአብሔር አለ ግን ሩቅ ነው ያለው የሚል ነው። ፍጥረተ አለሙን ፈጥሮ ለኛ ትቶታል፣ እኛ ነን የምናሽከረክረው ይላል።
🖊 Pantheism- እግዚአብሔርን በጣም ቅርብ ያደርገውና ሁሉ ነገር እግዚአብሔር ነው፣ ሁሉ ነገር አምላክ ነው ይላል። እኛ አምላክ ነን፣ ወንዙ፤ ሰማዩና ምድሩ አምላክ ነው ይላል።
የጸሎትን መንገድ የቀየረ ነው፤ ለምን ወይም ጠይቅ ሳይሆን እዘዝ ይላል።
አሁን ላይ አለምን የተቆጣጠረው ይህ ፍልስፍና ነው።
📖 ኢሳ 6:1
ቅዱስ ነው (ምጡቅ) ምድር ደግሞ በክብሩ ተሞልታለች (ቅርብ)።
3️⃣ እግዚአብሔርን የማወቅ ትርጉም
እግዚአብሔርን ማወቅ መረጃ ማወቅ አይደለም። ስለ እግዚአብሔር እያወቁ እግዚአብሔርን አለማወቅ ይቻላል።
እግዚአብሔርን ማወቅ የድርጅትና የቤተሰብ ጉዳይ አይደለም።
እግዚአብሔርን ማወቅ በግል ከእግዚአብሔር ጋር ያለ የፍቅር ግንኙነት ማለት ነው (ዘዳ 6:4)። እግዚአብሔርን ማወቅ የሁልጊዜ የፍቅር ግስጋሴ ነው።

Share:

Recommended...

የዮሐንስ ወንጌል ትምህርት 8

“Hiwot Tegelete” Gospel of John Chapter 2: Part 1 by Mamusha Fenta

...
Mamusha Fenta

1ኛ ቆሮንቶስ ትምህርት 35

Meskelun Menor by Mamusha Fenta on 1 Corinthians – Chapter 11 – Part 2 “መስቀሉን መኖር” 1ኛ ቆሮንቶስ : ምዕራፍ 11 – ክፍል 2 በማሙሻ ፈንታ

...
Mamusha Fenta

1ኛ ቆሮንቶስ ትምህርት 32

Meskelun Menor by Mamusha Fenta on 1 Corinthians – Chapter 10 – Part 2 “መስቀሉን መኖር” 1ኛ ቆሮንቶስ : ምዕራፍ 10 – ክፍል 3 በማሙሻ ፈንታ

...
Mamusha Fenta

Order Spiritual Maturity | A Book by Mamusha Fenta


Pickup location: Lighthouse Cafe, ACLA Church, Addis Ababa, Ethiopia

Filter by Preacher

Filter by Topic

Filter by Scripture

Filter by Resource Type

Resource Type

Filter by Series

Series