ከአምና…ዘንድሮ

Mamusha Fenta

Stream the sermon 

ከአምና…ዘንድሮ

Mamusha Fenta
Scripture: Romans 13

ሩቅ መንገድ ለመሔድ ተነስተን ስንጀምረው የሚደረስ አይመስልም። በመንገዳችን ዳር የተተከሉ የርቀት አመልካቾችም በጉዟችን ጅማሬ ላይ የሚያሳዩን ባለ ሦስትና አራት አሀዝ የኪሎ ሜትር ወይም ማይል ቁጥር ቶሎ መድረስ ለሚፈልግ መንገደኛ አታካች ናቸው። 

አንድ ሐቅ ግን ግልጽ ነው። አንድ ኪሎ ሜትር በነዳን ቁጥር ከሚቀረን ረጅሙ ርቀት ወስጥ አንድ ተቀንሷል። በሌላ አገላለጽ፡- ቅድም ከነበርንበት ርቀት በአንድ ኪሎ ሜትር  ወደ ፍጻሜያችን ተጠግተናል። ወደፊት በሔድን ቁጥር መድረሻችን ቀርቧል ማለት ነው።

ብዙ ጊዜ ባናስተውለውም ዘመንም እንዲሁ ነው። አንድ ዘመን በተጨመረልን ቁጥር ወደ ፍጻሜያችን በአንድ ዘመን ቀርበናል ማለት ነው። ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን ትላንት፣ ዛሬ፣ አምና፣ ዘንድሮ እያልን ስንቆጥር ወደ መጨረሻዉ (ወደ መዳናችን) እየተጠጋን ነው:- “ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና” ይላል (ሮሜ 13፡11)።  ደግሞም “…የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል” (1ጴጥ 4፡7) ብሎ ያሳስበናል።

በርግጥ ይህ እውነት ተዘጋጅተው ለሚኖሩ የሚያናውጥ ወይም አስደንጋጭ ሊሆን አይገባም (2ተሰ 2፡12)። ነገር ግን በማቴ 25 ላይ እንደ ተጠቀሱት በደንብ እስከ መጨረሻ ያልተዘጋጁ አምስቱ ሙሽራ ጠባቂ ቆነጃጅት የማንቂያ ደወል ነው። እንቅልፍ እንቅልፍ ባለን ጊዜ ማሰብ ያለብን እውነት ከትላንት ይልቅ ዛሬ እየተጠጋን መሆናችንን ነው። የማንቀላፋትና የለዘብተኝነት ዘመን አይደለም።

በአገራችን ዘመን አቆጣጠር አዲስ አመት ልንቀበል ነው። ነገ ‘ዘንድሮ’ ይሆንና ዛሬ ደግሞ ‘አምና’ ይባላል። የሕይወት ዘመን መቁጠሪያችን አንድ አመት ወደ ፍጻሜያችን መጠጋታችንን ታበስራለች። ቀን መቁጠሪያው በአንድ አመት በጨመረ ቁጥር መጨረሻው በአንድ አመት መቅረቡን መገንዘብ ለብዙዎቻችን አዳጋች አይመስለኝም። እንግዲያውስ አዲሱን አመት ስናከብር ከአምና ይልቅ ዘንድሮ ወደ ፍጻሜው መጠጋታችንን እያሰብን ይሁን። ስለሆነም በደስታ፣ በናፍቆትና በንቃት የበለጠ የምንዘጋጅበት ዘመን መለወጫ ይሁንልን።

ከአምና ይልቅ ዘንድሮ መዳናችን ቀርቧል- እንግዲህ እንንቃ!

መልካም አዲስ ዓመት!

Share:

Recommended...

የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት 46

የማቴዎስ ወንጌል 9:18-34 (አማ 54) ይህንም ሲነግራቸው፥ አንድ መኰንን መጥቶ፡— ልጄ አሁን ሞተች፤ ነገር ግን መጥተህ እጅህን ጫንባት፥ በሕይወትም ትኖራለች፡ እያለ ሰገደለት።ኢየሱስም ተነሥቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተከተለው። እነሆም፥ ከአሥራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ደም የሚፈስሳት ሴት በኋላው ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤ በልብዋ፡— ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ፥ እድናለሁ፡ ትል ነበረችና። ኢየሱስም...

Nigussie Bulcha

1ኛ ቆሮንቶስ ትምህርት

Meskelun Menor by Mamusha Fenta on 1 Corinthians – Introduction “መስቀሉን መኖር” 1ኛ ቆሮንቶስ መግቢያ – በማሙሻ ፈንታ

...
Mamusha Fenta

ኤፌሶን ትምህርት 40

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:21 (አማ54) ለእያንዳንዳችሁ በክርስቶስ ፍርሃት የተገዛችሁ ሁኑ። Ephesians 5:21 (ESV) Submitting to one another out of reverence for Christ.

...
Mamusha Fenta

Order Spiritual Maturity | A Book by Mamusha Fenta


Pickup location: Lighthouse Cafe, ACLA Church, Addis Ababa, Ethiopia

Filter by Preacher

Filter by Topic

Filter by Scripture

Filter by Resource Type

Resource Type

Filter by Series

Series