የጸጋ ስጦታዎች (ክፍል 1)

ትምህርተ መንፈስ ቅዱስ

Mamusha Fenta

Stream the sermon 

የጸጋ ስጦታዎች (ክፍል 1)

ትምህርተ መንፈስ ቅዱስ

Mamusha Fenta

ትምህርተ መንፈስ ቅዱስ

የጸጋ ስጦታዎች (ክፍል 1)

ይህ ትምህርት እስካሁን ከተማርናቸው ትምህርቶች ለየት የሚያደርገው፥ እስካሁን ያየነው በእያንዳንዳችን የግል ሕይወት ውስጥ የግለሰቡን ማንነት ለማነጽ፤ ለመለወጥ መንፈስ ቅዱስ የሚሠራውን ነው ያየነው። መንፈስ ቅዱስ ሲመጣ እንደግል ዳግም ይወልደናል፣ በመንፈስ ያጠምቀናል፣ ሀይል ይሠጠናል። አሁን ግን መንፈስ ቅዱስ እንደግል ብቻ ሳይሆን በጋራም በአካል ውስጥ የሚሠራውን ሥራ ለማየት እንሞክራለን። አካሉን ለማነጽ፣ ቤተክርስቲያንን ለማነጽ፣ ወንጌልን ለማስኬድ መንፈስ ቅዱስ የሚሠራውን ሥራ፤ የጸጋ ስጦታዎች የምንላቸውን ለማየት እንሞክራለን።

የዚህ ትምህርት ዋና ትኩረት 1ቆሮ 12-14 ነው።

  • 📖 1ቆሮ 12:1-11

📌 መግቢያ:- እግዚአብሔር ሰጪ አምላክ

  • እግዚአብሔር ለጋሽ አምላክ ነው፣ የስስት አምላክ አይደለም። ነገሮችን በእጆቹ ይዞ ከእኛ የሚሰውር አይደለም።
    • 📖 ያዕ 1:17
  • ሁሉ ነገራችን የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። ስጦታ ያልተሰጠው ሰው የለም። እያንዳንዷ እስትንፋሳችን፣ ሕይወታችን፣ ኑሯችን፣ እያንዳንዱ ቀን የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።
  • ሰው አይታወቀው ይሆን እንጂ እግዚአብሔር እየሰጠ ነው። እኛ ሰዎች ተቀባይና የማያመሠግን ነን።
  • እግዚአብሔር ለሚያምነውም ለማያምነውም፣ ለጻድቃኑም ለኀጥአኑም ነው ስጦታ የሚሠጠው።
    • 📖 ሐዋ. ሥራ 14:17
    • 📖 መዝ 104
  • እግዚአብሔር የአንድ ኀይማኖት ብቻ ሳይሆን የፍጥረት መጋቢ ነው። እግዚአብሔር መስጠት ይወዳል። እንኳን ተጠይቆ ሳይጠየቅ የሚሠጥ አምላክ ነው።
    • 📖 ሐዋ ሥራ 17:24-28
  • አመሠገንን አላመሠገንን ተፈጥሯዊ ብቃቶቻችን፣ ችሎታዎቻችን የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው።
  • እግዚአብሔር ‘መንፈሳዊ’ ለምንላቸው ነገሮች በቂ ሆኖ ሰጪ፣ ‘Secular’ ለምንላቸው ደግሞ ሩቅ ሆኖ ታዛቢ አምላክ አይደለም፤ ሁሉን በሁሉ የሚሠራ አምላክ ነው።
    • 📖 ዘጸ 31:1-6
  • እግዚአብሔር አይወሰንም፤ የእለት ተእለት ሕይወታችን፣ እውቀታችን፣ ችሎታችን የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። የአመራር ጥበብን የሚሠጥ ነው።
    • 📖 ዘፍ 41:38 – ዮሴፍ
    • 📖 ዳን 1:17 – ዳንኤል
  • እግዚአብሔር ለክብሩ ተፈጥሮአዊ ችሎታን የሚሠጥ ነው።
  • ትልቁንም ስጦታ የሰጠን እግዚአብሔር ነው። አንድያ ልጁን እስኪሠጥ ድረስ አለሙን የወደደበትን የመጨረሻ ትልቁን ስጦታ የሰጠን እግዚአብሔር ነው። በሱ አማካኝነት የዘላለም ሕይወትን ሰጠን።
    • 📖 ሮሜ 6:23
  • የጸጋ ስጦታ ሲባል የዘላለም ሕይወትን አስባችሁ ታውቃላችሁ?
  • “ጌታን ተቀበሉ” የምንለው ስጦታ ስለሆነ ነው፤ የእኛ ስላልሆነ ነው።
  • የዘላለም ሕይወት፣ የልጅነት መብት የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።
  • እግዚአብሔር የተለዩ ስጦታዎችን ይሰጣል።
  • አማኞችን በአጠቃላይ እንዲያገለግሉ የሚያበቁ የተለዩ ስጦታዎችን ይሰጣል።
  • የተወሰኑ ሰዎች መድረክ ላይ ወጥተው ስላገለገሉ ብቻ የተለየ ከፍታ ለራሳቸው ሰጥተው ሌሎቻችን ተሳታፊ የሆንን ከመሠለን ተሳስተናል። ‘ተሳታፊ” የአካል ብልቶች አሉን? አካል ውስጥ ተከታታይ የለም።
  • ቤተክርስቲያን ጥቂቶች ብቻ የሚጫወቱባት ሜዳ አይደለችም፣ ሁሉም በጸጋ ተሞልቶ የሚያገለግልባት ናት።
    • 📖 ኤፌ 4:11 …ለእያንዳንዳችን ጸጋ ተሰጠን
  • እግዚአብሔር ሐዋርያት፣ ነቢያት፣ ወንጌል ሰባኪያን፣ እረኞችንና አስተማሪዎችን የሰጠው ቅዱሳንን እንዲያገለግሉ ያስታጥቋቸው ዘንድ ነው። እነዚህ አሰልጣኞች፣ አስታጣቂዎች ናቸው።
  • አማኞች በአጠቃላይ እንድናገለግል እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ የሚሠጣቸው ተአምራዊ ብቃቶች አሉ። ከሰው ችሎታ ውጪ የሆነ፣ ከተፈጥሮ ችሎታ ውጪ የሆነ፣ በስልጠና ያልዳበረ እግዚአብሔር የሚያፈሰው super natural የሆነ ተአምራዊ ብቃቶችን እግዚአብሔር ይሰጣል።
  • ሁሉ ሰው ያገለግላል፣ ሁሉ ጸጋ ተሰጥቶታል ስንል ሁሉ ሰው መሪ ነው ማለት ግን አይደለም። ሁላችን እንድናገለግል ሐዋርያት፣ ነቢያት፣ ወንጌል ሰባኪያን፣ እረኞችና አስተማሪዎች ያስታጥቁናል።
  • እግዚአብሔር አካል በሙሉ እንዲያገለግል የተለዩ፣ ከመንፈስ ቅዱስ የሆኑ የጸጋ ስጦታዎች ተአምራዊ ብቃቶችን ይሠጣል።
    • 📖 1ቆሮ 12:
  • የጸጋ ስጦታን በሰው ብቃትና ችሎታ ከሚተካ አስተሳሰብ መጠበቅ አለብን።
  • የመንፈስ ቅዱስን ምሪት በስልታዊ እቅድ ከመተካት መቆጠብ አለብን።
  • ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ጉብኝት ከተለያት ባዶ ሕንጻ ትሆንና ቱሪስት የሚጎበኛት ትሆናለች።
  • እግዚአብሔር በሚሰጠን ጸጋ ካላገለገልን፣ ካልተነዳን፣ በመንፈስ ሙቀት ከሌለ በስልታዊ እቅድ ብቻ ማገልገል አንችልም።
  • የጸጋ ስጦታዎች አማኞችን በሙሉ የተመለከቱ ናቸው።
    • 📖 ዘሁ 11:29
  • ሀጢአት ስላላተወገደ በሁሉ ላይ መንፈስ አልፈሰሰም ነበረ።
    • 📖 ኢዩ 2:28-29

📌 የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ባህሪያቸው (1ቆሮ 12 )

1) መንፈሳዊ ስጦታዎች (ኒውማቲካ) ይባላሉ (12:1)

  • ተፈጥሯዊ አይደሉም፤ ለምሳሌ በልሳን መናገር
  • በትምህርት፣ በችሎታ እና በልምድ የዳበሩ አይደሉም
  • መንፈስ ቅዱስ የሚሠጣቸው ናቸው

2) የጸጋ ስጦታዎች ይባላሉ (12:4)

  • ካሪዝማታ ይባላሉ
  • ነጻ ስጦታ፣ ለማይገባቸው የተሰጡ፣
  • በጸጋ ለማገልገል የተለየ ሰው መሆን አይጠበቅብንም።
  • የጸጋ ስጦታ የጸጋ መሆኑን መረዳት እግዚአብሔር ሲሠራብን ክብር ለመስጠት ይመቻል። ብቃት እንዳለን ካሰብን፣ ስለመጠንን የተሰጠን ከመሰለን አረማመዳችን ይቀየራል። ስጦታው የኛ ግን አይደለም፤ ሳይገባን የተሰጠን እንጂ።
  • የሚያገለግሉ ሰዎች ላይ የተለየ expectations አለን። ኑሮ መኖር ያለብን የጌታ ልጆች ስለሆንን ብቻ ነው፤ አገልግሎትማ የጸጋ ነው። ኑሮዬን አሻሽዬ የምቀበለው አይደለም።
  • ሰው በእግዚአብሔር ፊት በፈሪሃ እግዚአብሔር መኖር ያለበት ሲያገለግል ብቻ አይደለም።
  • የጸጋ ስጦታ መኖር የጽድቅና የቅድስና ምልክት አይደለም፣ የኑሮ expectation አይደለም።

📌 ዐላማቸው

  • በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ የጸጋ ስጦታን ትክክለኛ ላልሆነ ዐላማ ማዋል ይቻላል። (ሐዋ ሥራ 8-ሲሞን)
  • የጸጋ ስጦታዎች የሚገለጡት ኢየሱስን በማክበር ነው፤ አላማቸው እንደዚህ ነው የሚፈጸመው።
    • 📖 ዮሐ 16:14
    • 📖 1ቆሮ 12:1-3
  • ሰው በመንፈስ ሲያገለግል ዋና አላማው ኢየሱስ ጌታ ነው ማለት ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ጌትነት ነው የጸጋ ስጦታ መነሻው።

Share:

Recommended...

1ኛ ቆሮንቶስ ትምህርት 13

Meskelun Menor by Mamusha Fenta on 1 Corinthians – Chapter 5 – Part 3 “መስቀሉን መኖር” 1ኛ ቆሮንቶስ : ምዕራፍ 5 – ክፍል 3 በማሙሻ ፈንታ

...
Mamusha Fenta

የዮሐንስ ወንጌል ትምህርት 47

Hiwot Tegelete” John Chapter 12 Part 5 by Mamusha Fenta

...
Mamusha Fenta

የዮሐንስ ወንጌል ትምህርት 53

Hiwot Tegelete” John Chapter 14 Part 2 by Mamusha Fenta

...
Mamusha Fenta

Order Spiritual Maturity | A Book by Mamusha Fenta


Pickup location: Lighthouse Cafe, ACLA Church, Addis Ababa, Ethiopia

Filter by Preacher

Filter by Topic

Filter by Scripture

Filter by Resource Type

Resource Type

Filter by Series

Series