የሱስም እነዚህን ቃሎች ሁሉ በፈጸመ ጊዜ፥ ለደቀ መዛሙርቱ። ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካ እንዲሆን ታውቃላችሁ፥ የሰው ልጅም ሊሰቀል አልፎ ይሰጣል አለ። በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ፥ ኢየሱስንም በተንኰል ሊያስይዙት ሊገድሉትም ተማከሩ፤ ነገር ግን። በሕዝቡ ዘንድ ሁከት እንዳይነሣ በበዓል አይሁን አሉ። ኢየሱስም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቱ የሞላው የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች በማዕድም ተቀምጦ ሳለ በራሱ ላይ አፈሰሰችው። ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው ተቈጡና። ይህ ጥፋት ለምንድር ነው? ይህ በብዙ ዋጋ ተሽጦ ለድሆች ሊሰጥ ይቻል ነበርና አሉ። ኢየሱስም ይህን አውቆ እንዲህ አላቸው። መልካም ሥራ ሠርታልኛለችና ሴቲቱንስ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ? ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፥ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም፤ እርስዋ ይህን ሽቱ በሰውነቴ ላይ አፍስሳ ለመቃብሬ አደረገች። እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ወንጌል በዓለም ሁሉ በማናቸውም ስፍራ በሚሰበክበት እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል። በዚያን ጊዜ የአስቆሮቱ ይሁዳ የሚባለው ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ወደ ካህናት አለቆች ሄዶ። ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ? እነርሱም ሠላሳ ብር መዘኑለት። ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ አሳልፎ ሊሰጠው ምቹ ጊዜ ይሻ ነበር።
When Jesus had finished saying all these things, he said to his disciples, “As you know, the Passover is two days away—and the Son of Man will be handed over to be crucified.” Then the chief priests and the elders of the people assembled in the palace of the high priest, whose name was Caiaphas, and they schemed to arrest Jesus secretly and kill him. “But not during the festival,” they said, “or there may be a riot among the people.” While Jesus was in Bethany in the home of Simon the Leper, a woman came to him with an alabaster jar of very expensive perfume, which she poured on his head as he was reclining at the table. When the disciples saw this, they were indignant. “Why this waste?” they asked. “This perfume could have been sold at a high price and the money given to the poor. Aware of this, Jesus said to them, “Why are you bothering this woman? She has done a beautiful thing to me. The poor you will always have with you, but you will not always have me. When she poured this perfume on my body, she did it to prepare me for burial. Truly I tell you, wherever this gospel is preached throughout the world, what she has done will also be told, in memory of her.” Then one of the Twelve—the one called Judas Iscariot—went to the chief priests and asked, “What are you willing to give me if I deliver him over to you?” So they counted out for him thirty pieces of silver. From then on Judas watched for an opportunity to hand him over.