ክርስቶስ ኢየሱስን ምን ላድርገው

የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት 121

Nigussie Bulcha

Stream the sermon 

ክርስቶስ ኢየሱስን ምን ላድርገው

የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት 121

Nigussie Bulcha

ኢየሱስም በገዢው ፊት ቆመ፤ ገዢውም። የአይሁድ ንጉሥ አንተ ነህን? ብሎ ጠየቀው፤ ኢየሱስም። አንተ አልህ አለው። የካህናት አለቆችም ሽማግሎችም ሲከሱት ምንም አልመለሰም። በዚያን ጊዜ ጲላጦስ። ስንት ያህል እንዲመሰክሩብህ አትሰማምን? አለው። ገዢውም እጅግ እስኪደነቅ ድረስ አንዲት ቃል ስንኳ አልመለሰለትም። በዚያም በዓል ሕዝቡ የወደዱትን አንድ እስረኛ ሊፈታላቸው ለገዢው ልማድ ነበረው። በዚያን ጊዜም በርባን የሚባል በጣም የታወቀ እስረኛ ነበራቸው። እንግዲህ እነርሱ ተሰብስበው ሳሉ ጲላጦስ። በርባንን ወይስ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ? አላቸው፤ በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና። እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ። ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ ብላ ላከችበት። የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ግን በርባንን እንዲለምኑ ኢየሱስን ግን እንዲያጠፉ ሕዝቡን አባበሉ። ገዢውም መልሶ። ከሁለቱ ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ? አላቸው፤ እነርሱም። በርባንን አሉ። ጲላጦስ። ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው? አላቸው፤ ሁሉም። ይሰቀል አሉ። ገዢውም። ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው? አለ፤ እነርሱ ግን። ይሰቀል እያሉ ጩኸት አበዙ። ጲላጦስም ሁከት እንዲጀመር እንጂ አንዳች እንዳይረባ ባየ ጊዜ፥ ውኃ አንሥቶ። እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ እናንተ ተጠንቀቁ ሲል በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ። ሕዝቡም ሁሉ መልሰው። ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን አሉ። በዚያን ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፥ ኢየሱስን ግን ገርፎ ሊሰቀል አሳልፎ ሰጠ። በዚያን ጊዜ የገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ውስጥ ወሰዱት ጭፍራውንም ሁሉ ወደ እርሱ አከማቹ። ልብሱንም ገፈው ቀይ ልብስ አለበሱት፥ ከእሾህም አክሊል ጎንጉነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፥ በፊቱም ተንበርክከው። የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ ዘበቱበት፤ ተፉበትም መቃውንም ይዘው ራሱን መቱት። ከዘበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፥ ልብሱንም አለበሱት ሊሰቅሉትም ወሰዱት።

Meanwhile Jesus stood before the governor, and the governor asked him, “Are you the king of the Jews?” “You have said so,” Jesus replied. When he was accused by the chief priests and the elders, he gave no answer. Then Pilate asked him, “Don’t you hear the testimony they are bringing against you?” But Jesus made no reply, not even to a single charge—to the great amazement of the governor. Now it was the governor’s custom at the festival to release a prisoner chosen by the crowd. At that time they had a well-known prisoner whose name was Jesus Barabbas. So when the crowd had gathered, Pilate asked them, “Which one do you want me to release to you: Jesus Barabbas, or Jesus who is called the Messiah?” For he knew it was out of self-interest that they had handed Jesus over to him. While Pilate was sitting on the judge’s seat, his wife sent him this message: “Don’t have anything to do with that innocent man, for I have suffered a great deal today in a dream because of him.” But the chief priests and the elders persuaded the crowd to ask for Barabbas and to have Jesus executed. “Which of the two do you want me to release to you?” asked the governor. “Barabbas,” they answered. “What shall I do, then, with Jesus who is called the Messiah?” Pilate asked. They all answered, “Crucify him!” “Why? What crime has he committed?” asked Pilate. But they shouted all the louder, “Crucify him!” When Pilate saw that he was getting nowhere, but that instead an uproar was starting, he took water and washed his hands in front of the crowd. “I am innocent of this man’s blood,” he said. “It is your responsibility!” All the people answered, “His blood is on us and on our children!” Then he released Barabbas to them. But he had Jesus flogged, and handed him over to be crucified. Then the governor’s soldiers took Jesus into the Praetorium and gathered the whole company of soldiers around him. They stripped him and put a scarlet robe on him, and then twisted together a crown of thorns and set it on his head. They put a staff in his right hand. Then they knelt in front of him and mocked him. “Hail, king of the Jews!” they said. They spit on him, and took the staff and struck him on the head again and again. After they had mocked him, they took off the robe and put his own clothes on him. Then they led him away to crucify him.

Share:

Recommended...

ኤፌሶን ትምህርት 13

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:11–22 (አማ54) ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ በሥጋ አሕዛብ የነበራችሁ፥ በሥጋ በእጅ የተገረዙ በተባሉት ያልተገረዙ የተባላችሁ፥ ይህን አስቡ፤ በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ። አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።...

Mamusha Fenta

የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት 4

የማቴዎስ ወንጌል 2:13-15 (አማ54) እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ። ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ፡ አለው። እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ። ልጄን ከግብፅ ጠራሁት፡ የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብፅ ሄደ፥ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ...

Mamusha Fenta

የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት 58

ማቴዎስ 12: 22-37 (አማ 54) ከዚህም በኋላ ጋኔን ያደረበትን ዕውር ዲዳም ወደ እርሱ አመጡ፤ ዕውሩም ዲዳውም እስኪያይና እስኪናገር ድረስ ፈወሰው። ሕዝቡም ሁሉ ተገረሙና፦ እንጃ ይህ ሰው የዳዊት ልጅ ይሆንን? አሉ። ፈሪሳውያን ግን ሰምተው፦ ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም አሉ። ኢየሱስ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት...

Nigussie Bulcha

Order Spiritual Maturity | A Book by Mamusha Fenta


Pickup location: Lighthouse Cafe, ACLA Church, Addis Ababa, Ethiopia

Filter by Preacher

Filter by Topic

Filter by Scripture

Filter by Resource Type

Resource Type

Filter by Series

Series