የሥላሴ ትምህርት ክፍል 2

ትምህርተ እግዚአብሔር

Mamusha Fenta

Stream the sermon 

የሥላሴ ትምህርት ክፍል 2

ትምህርተ እግዚአብሔር

Mamusha Fenta
Scripture: Jude, New Testament

ትምህርተ ሥላሴ (ክፍል 2)

📍 የሥላሴ አካላት ግንኙነት

አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስን በተመለከተ ሥላሴን የማያምኑ ሰዎችየሦላሴ አማኞችን ለማሸማቀቅ የሚሞክሩበት አንዱ ነገር ግንኙነታቸውን በማንሳት ነው። እንዴት ነው ሆኖ ነው ኢየሱስን ከአብ እኩል አምላክ ነው የምትሉት? “አብ ልኮኛል፣ የሱን ፈቃድ ነው ለመፈጸም የመጣሁት፣ ከራሴ አይደለም እሱ ነው የላከኝ” እያለ እንዴት ተላኪ ከላኪው ጋር እኩል ይሆናል? ይላሉ።

1️⃣ የባህርይ (ማንነት) እኩልነት

  • የሥላሴ አካላት ማንነትን በተመለከተ እኩል/አንድ ናቸው።
  • በሥላሴ አካላት መካከል በጣም አምላክ የለም፣ ዝቅ ያለም አምላክ የለም፤ አንድ ናቸው።
  • በመለኮት ማንነት እኩል ናቸው።

2️⃣ የተግባር (ግብር) እኩልነት

  • የሥላሴ አካላት የሥራ /የተግባር ልዩነት አላቸው። የየራሳቸውን ግብር ነው የሚፈጽሙት።
  • የማንነት እኩልነት ፥ የግብር ልዩነት አላቸው።
  • በተለያየ መንገድ ከፍጥረት ጋር ይገናኛሉ።

🖊 ፍጥረት (CREATION)

  • የእግዚአብሔር ሥራ ነው (ዘፍ 1:1)
  • እዛው የፍጥረትን ሥራ በዝርዝር ስናይ ግን የሥላሴን ተግባር በውስጡ እናያለን። “እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ…..የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሃው ላይ ይሰፍፍ/ይረብብ ነበር”
  • ሥራው አንድ ነው እያንዳንዳቸው ግን የየራሳቸው ROLE አላቸው።
  • እግዚአብሔር “ይሁን ይሁን” እያለ ሲፈጥር የእግዚአብሔር መንፈስ እያጸና የፍጥረትን ሥራ ይሠራል።
  • እግዚአብሔር የሚናገረው ቃል ደግሞ ዝም ብሎ ቃል እንዳልሆነ ደግሞ አዲስ ኪዳን ይነግረናል። ያ ቃል ህያው ቃል ነው፣ ሎጎስ ነው።
  • 📖 ዮሐ 1:3
  • ሎጎስ:- እሱ ምክንያት የሌለው ነገሮችን በሙሉ ያመጣቸው ነው።
  • በግሪክ ፍልስፍና ነገሮች ዝም ብለው አይመጡም፤ ያመጣቸው ኃይል አለ ብለው ያምናሉ ያንንም ሎጎስ ይሉታል።
  • ዮሐንስ ግን ይሄ ሁሉ ነገር ከመሆኑ በፊት ሎጎስ (beginning of logos) ነበረ ይላቸዋል። እሱ HE እያለ ይጠራዋል (person ያደርገዋል። እነሱ ግን IT ይሉታል ኃይል ነው ስለሚሉ።
  • ይሔ ሎጎስ እግዚአብሔር ነበረ፤ አምላክ ነበረ ይልና ሁሉ በእርሱ ተፈጠረ ከተፈጠረው ሁሉ ያለርሱ የተፈጠረ የለም ይላል።
  • የሚታየውን የማይታየውን፤ በሰማይ ያለውን በምድር ያለውን በሙሉ፤ የተፈጠረውን በሙሉ የፈጠረው ያ ሎጎስ ነው።
  • ያ በፍጥረት ሥራ ላይ “ይሁን ይሁን” ዝም ብሎ አይደለም፤ ሎጎስ ነው፤ እሱም እግዚአብሔር ወልድ ነው።
  • እግዚአብሔር አብ ፈጣሪ ነው፣ እግዚአብሔር ወልድ ፈጣሪ ነው፣ እግዚአብሔር መንፈስ ፈጣሪ ነው። በፍጥረት ሥራ ውስጥ ግን የተለያየ ግብር አላቸው። አብ ይናገራል፣ ወልድ እያደረገው ነው፣ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ እያጸናው ነው።
    • 📖 ቆላ 1:15-16
  • እርሱ የፍጥረት ሁሉ በኩር ነው፤ በፍጥረት ሁሉ ላይ በኩር ነው።
    • 📖 ዕብ 1:2
  • እግዚአብሔር አለማትን በልጁ ፈጠረ።
    • 📖 መዝ 33:6

🖊 ድነት (SALVATION)

  • ማዳን የእግዚአብሔር ነው።
    • 📖 መዝ 3:8
  • በመዳን ሒደት ውስጥ ግን ሚናቸው ይለያይ እንጂ የሁሉም የሥላሴ አካላት አሉ።
  • የእግዚአብሔር አብ እቅድን፣ ፈቃድን፣ ስጦታ ሰጪነትን እናያለን፤ ይህ የእግዚአብሔር አብ ሚና ነው።
    • 📖 ዮሐ 3:16
    • 📖 ገላ 4:4
  • ፍጥረትም መዳናችንም ሥላሴአዊ ነው።

* የወልድ መስዋዕትነት (ሚና)

  • መምጣት
  • መሞት
    • 📖 ኤፌ 5:2
  • ወልድ በደስታ ራሱን ሰጠ።
    • 📖 ቲቶ 2:14

* የመንፈስ ቅዱስ መስዋዕትነት (ሚና)

  • መዳንን በሰዎች ሕይወት ውስጥ የሚሠራው መንፈስ ቅዱስ ነው።
  • ዳግም ልደትን፣ አዲስ ማንነትን የሚሠጠው መንፈስ ቅዱስ ነው። ቅድስናን፣ ሕይወትን የሚሠጠው መንፈስ ቅዱስ ነው።
    • 📖 ዮሐ 3:5-8
    • 📖 ሮሜ 8:13
  • አንድ አምላክ/አንድ መዳን የተለያየ ሚና!
    • 📖 1 ጴጥ 1:1-2

3️⃣ የግብር መገዛት (FUNCTION)

  • በዚህ የግብር ልዩነት ውስጥ መገዛዛት አለ። እኩልነት አለ፤ የተለያየ ግብር አለ፣ መገዛዛት አለ። አንዱ ላንዱ ይገዛል፣ ይላካል። መላክ አለ፣ መ’ላክ አለ፣ የአብ ፈቃድ አለ፣ ፈቃዱን ለማድረግ ነው የመጣሁት አለ።
  • በፍጥረትም በማዳንም አብ ይልካል፣ ወልድ ተልኳል።
    • 📖 ዮሐ 6:38
    • 📖 ፊል 2:8
  • እኩልነትን ሳይደመስስ አዛዥ አለ ታዛዥ አለ።
  • በሥላሴ አካላት ውስጥ ONTOLOGICAL EQUALITY & FUNCTIONAL SUBORDINATION አለ።
  • መገዛት/ ዝቅ ማለት ማነስን አያመለክትም።
  • እመቤትና ጌታ እኩል ነው? አባትና ልጅ እኩል ነው? አሠሪ ‘የበለጠ ሰው’ ነው? ሠራተኛስ ‘ያነሰ ሰው’ ነው? አይደለም። በግብር መገዛት ማነስን አያመለክትም።
  • አባትና ልጅ በማንነት እኩል ናቸው፤ በግብር ግን አባት ያዛል ልጅ ይታዘዛል።

🖊 III. ውዝግቦችና የቤተክርስቲያን አቋም

1) ሴባልያኒዝም

  • ሰባልዮስ አንድ ማንነት አንድ አካል ብሎ ነው ያስተማረው።
  • ይህም ትምህርቱ Monarchial Modalism ይባላል። ይህም ማለት አንድ አምላክ በተለያየ መልክ(mode) ነው የተገለጠው ማለት ነው።
  • “በብሉይ ኪዳን አብ የነበረው በአዲስ ኪዳን ወልድ(ኢየሱስ) ሆኖ ተገልጧል” ብሎ አስተምሯል።

ይህን ትምህርት ቤተክርስቲያን እንዲህ በሚል አቋም አውግዛለች

  • “አካላቱን ሳንደባልቅ፤ ህላዌን ሳይከፍል፤ አንዱን አምላክ በሦስትነት፤ ሦስትን በአንድነት እናመልካለን።”

2) አርዮሳዊያን

  • ይህ ትምህርት የተጀመረው በአርዮስ ነው።
  • አርዮስ የወልድን አምላክነት የካደ ሰው ነው። “ወልድ ያልነበረበት ጊዜ አለ” ብሎ ያምናል።
  • “ወልድ ዓለማትን ለመፍጠር የተፈጠረ ነው” ብሎ አስተምሮ ነበር።
  • አርዮስ በ325 ዓ.ም በኒቅያ ጉባኤ ሐሰተኛ አስተማሪ ትምህርቱም ኑ ፋቄ ተብሎ ተወግዟል።

እንዲህ ብላ ነበር ቤተክርስቲያን ያወገዘችው:-

“ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ፤ ቀዳሚና ተከታይ የሌለው የአብ ልጅ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ እናምናለን። እርሱም ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ፤ የተፈጠረ ያይደለ የተወለደ ፤ በመለኮት ከአብ ጋር የሚስተካከል ነው።”

Share:

Recommended...

1ኛ ዮሐንስ ትምህርት 1

1ኛ ዮሐንስ መልእክት በማሙሻ ፈንታ – ምዕራፍ 1 ክፍል 1 (1John Chapter 1 Part 1 by Mamusha Fenta)

...
Mamusha Fenta

ኤፌሶን ትምህርት 56

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6:13–17 (አማ54) ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ። – እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤ በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ...

Aberham Teklemariam

የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት - 18

ማቴዎስ 5:33-37(አማ54) “ደግሞ ለቀደሙት፦ በውሸት አትማል ነገር ግን መሐላዎችህን ለጌታ ስጥ እንደተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፦ ከቶ አትማሉ፤ በሰማይ አይሆንም የእግዚአብሔር ዙፋን ነውና፤ በምድርም አይሆንም የእግሩ መረገጫ ናትና፤ በኢየሩሳሌምም አይሆንም የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናትና፤ በራስህም አትማል፥ አንዲቱን ጠጉር ነጭ ወይም ጥቁር ልታደርግ አትችልምና። ነገር ግን ቃላችሁ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፤ ከነዚህም የወጣ...

Mamusha Fenta

Order Spiritual Maturity | A Book by Mamusha Fenta


Pickup location: Lighthouse Cafe, ACLA Church, Addis Ababa, Ethiopia

Filter by Preacher

Filter by Topic

Filter by Scripture

Filter by Resource Type

Resource Type

Filter by Series

Series