የቃሉ ትክክለኛነት

ትምህርተ መፅሐፍ ቅዱስ ክፍል 2

Mamusha Fenta

Stream the sermon 

የቃሉ ትክክለኛነት

ትምህርተ መፅሐፍ ቅዱስ ክፍል 2

Mamusha Fenta

የእግዚአብሔር ቃል ትክክለኛነት (እውነተኛነት)

📖 መዝ 119:41-48፣, 97-104፣ 129-136

  • የእግዚአብሔር ቃል የሚናገረው ሐቅ ነው፣ ከስህተት የጸዳ ነው፣ ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ነው፣

🏷 ጥቂት አስረጂዎች:-
መጽሐፍ ቅዱስ ሲጻፍ የተጻፉባቸው ረቂቆች፣ ከዚያ በኋላ ደግሞ በመጡ ብዙ ሺህ ቅጂዎች፥ (የመጀመሪያዎቹ ረቂቆች) አሉ፤ እነኚህ በሙሉ እግዚአብሔር አለባቸው። ትክክለኛ እግዚአብሔር ማለት የፈለገውን የሚሉ ናቸው።
እግዚአብሔር ሰዎችን ተጠቅሟል፤ ሰዎች ሲጽፉ፣ ኮፒ ሲያደርጉ፣ ሲተረጉሙ እግዚአብሔር የፈለገውን ነው የሚሉት።
ትክክለኛ ማለት ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ማለት የፈለገው ነው።
በጥንቃቄ የተጻፉትና የተተረጎሙት ቅዱሳት መጻሐፍት በሙሉ እግዚአብሔር የፈለገውን የሚናገሩ ናቸው።
እግዚአብሔር ለማለት የፈለገውን ከተረዳን ግጭት የለም፣ ስህተት የለም፤ ትክክለኛ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ በትክክል ሲተረጎም እግዚአብሔር ማለት የፈለገውን በመናገር ስህተት አልባ ነው።
የተጻፈን ነገር አንብቦ ብቻ ጸሐፊው ምን ለማለት እንደፈለገ መረዳት ጥንቃቄ ይጠይቃል።

🏷 ጥቂት ማስረጃዎች
1) ከእስትንፋሰ መለኮት (INSPIRATION) አንጻር
የሚያስረዳን የእግዚአብሔር ቃል ስህተት አልባ መሆኑን ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው፤ “ቃሉ ያለው፤ አምላክ ያለው”
📖 ኢሳ 7:14______📖 ማቴ 1:22
📖 ዘፍ 2:24______📖 ማቴ 19:4-5


2) ከእግዚአብሔር ባህሪ አንጻር
ቃሉ የእግዚአብሔር ባህርይ አለበት። እግዚአብሔር ደግሞ በባህሪው አይዋሽም።
እግዚአብሔር ያለው ሁሌ ልክ ነው። ስህተት አልባ ነው።
ቃሉ እግዚአብሔር የሚለው ነው፤ ቃሉ ደግሞ የተናጋሪውን ባህሪ ይዟል፤ እርሱም ደግሞ እግዚአብሔር አይዋሽም፣ ስህተት አልባ ነው።
እግዚአብሔር እያለ ያለውን ካገኘነው እውነት ነው።
📖 ዘሁ 23:19
📖 ቲቶ 1:1-2
📖 መዝ 12:6
📎 መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ፤ ቃሉ ያለው አምላክ ያለው ስለሆነ፤ አምላክ ጋር ደግሞ ስህተት ስለሌለ መጽሐፍ ቅዱስ ከስህተት የጸዳ ነው።


3) ከኢየሱስ ምስክርነት አንጻር
ኢየሱስ እውነት ብቻ ሳይሆን የእውነት መለኪያም እርሱ ራሱ ነው።
አንድም ቦታ ኢየሱስ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማስተካከል/ለማረም ሲሞክር አናገኘውም። አገልግሎቱን ሲጀምር የብሉይ ኪዳንን መጽሐፍ ዘርግቶ ነው የጀመረው። ሰበከው እንጁ ለማስተካከል አልሞከረም። ለምን? ቃሉ ያለው፤ አምላክ ያለው!
📖 ዮሐ 17:17
📖 ማቴ 5:18
📖 ማቴ 24:35
📖 ሉቃ 24:44
በኢየሱስ የተጻፈው ይፈጸማል እንጂ ይስተካከል የለም።


4) የትንቢት ፍጻሜዎች
የቃሉን ትክክለኛነት በትንቢት ፍጻሜ ማወቅ ይቻላል። እግዚአብሔር ስለ ነቢያት መለኪና ሲናገር፥ አንድ ነቢይ ትንቢት ቢናገርና የተናገረው ባይፈጸም ውሸት ነው ማለት ነው ይላል።
እግዚአብሔር የተናገረው ሐቅ ስለሆነ ያለው ይፈጸማል።
እግዚአብሔር ተናግሮ የማይፈጸም የለም፤ ካልተፈጸመ ተናጋሪው ዋሽቷል ማለት ነው።
📖 ኢሳ 44:28 ፣ 45:1
📖 እዝራ 1:1-3
📖 ኢሳ 7:14
📖 ማቴ 1:22-23


🏷 መሳይ ተቃርኖዎችስ?
ተቃርኖዎች ሲነሱ መደንገጥ አያስፈልግም፤ ምክንያቱም:-
🖊 ጥቂት ስለሆኑ
🖊 መጽሐፍ ቅዱስ በሰውኛ ዘይቤ የተጻፈ ስለሆነ
እነዚህ የሚቃረኑ የሚመስሉ ሀሳቦች የሚመጡበት ምክንያቶች:-
1) የመረዳት ውሱንነት
2) የትኩረት ልዩነቶች
3) የዐውድ ልዩነቶች
📖 ምሳ 26:4-5
መረዳት ይጠይቃል እንጂ የእግዚአብሔር ቃል እርስ በርሱ የሚጋጭ አይደለም።


🏷 ማጠቃለያ:- መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ የተጻፈ ትክክለኛ፣ ከስህተት የጸዳ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን እናምናለን!

Share:

Recommended...

1ኛ ቆሮንቶስ ትምህርት 29

Meskelun Menor by Mamusha Fenta on 1 Corinthians – Chapter 9 – Part 2 “መስቀሉን መኖር” 1ኛ ቆሮንቶስ : ምዕራፍ 9 – ክፍል 2 በማሙሻ ፈንታ

...
Mamusha Fenta

እንግዲህ ሂዱ

የዮሐንስ ወንጌል 4:1-15 (አማ54) እንግዲህ። ኢየሱስ ከዮሐንስ ይልቅ ደቀ መዛሙርት ያደርጋል ያጠምቅማል ማለትን ፈሪሳውያን እንደ ሰሙ ጌታ ባወቀ ጊዜ፥ ይሁዳን ትቶ ወደ ገሊላ ደግሞ ሄደ፤ ዳሩ ግን ደቀ መዛሙርቱ እንጂ ኢየሱስ ራሱ አላጠመቀም። በሰማርያም ሊያልፍ ግድ ሆነበት። ስለዚህ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ስፍራ አጠገብ ወደምትሆን ሲካር ወደምትባል የሰማርያ ከተማ መጣ፤...

Mamusha Fenta

የዮሐንስ ወንጌል ትምህርት 27

“Hiwot Tegelete” John Chapter 8: Part 3 by Mamusha Fenta

...
Mamusha Fenta

Order Spiritual Maturity | A Book by Mamusha Fenta


Pickup location: Lighthouse Cafe, ACLA Church, Addis Ababa, Ethiopia

Filter by Preacher

Filter by Topic

Filter by Scripture

Filter by Resource Type

Resource Type

Filter by Series

Series