የእግዚአብሔር ባሕርያት ክፍል 1 (Attributes of God Part 1)
እግዚአብሔርን የምናውቅበት አንዱ መንገድ ባህርያቱን ማወቅ ነው። ባሕርያቱን ባወቅን ቁጥር እግዚአብሔርን እናውቀዋለን።
1) ትርጉም
የእግዚአብሔር ባሕርያት (ATTRIBUTES of GOD) ጊዜያዊ ጠባዮች ሳይሆኑ የማንነቱ መገለጫዎች ማለታችን ነው።
2) አንድነት 📖 ዘጸ 34:5-7
- የእግዚአብሔር ባሕርያት ዝርዝራቸው በጣም ብዙ ናቸው፤ አንድነታቸውን (UNIFIED) ግን ማሠብ አለብን። በጣም ብዙ ናቸው ግን የአንድ አምላክ መገለጫዎች ናቸው። እግዚአብሔር የባሕርያቱ ግጥምጥሞች አይደለም።
- ባሕርያቱ በሙሉ የማንነቱ/የክብሩ መገለጫዎች ናቸው፤ አንድ ናቸው አይነጣጠሉም።
- የአምላክ መገለጫ ባሕርያት ሁሉም በአንድ ጊዜ ናቸው። እግዚአብሔር ባሕርያት ጋር “ብቻ” አይሠራም።
- የእግዚአብሔርን ባሕርያት በትክክል ካላወቅን በትክከል ልናመልከው፣ በትክክል ለመኖር አንችልም።
3) አከፋፈላቸው (ለጥናት እንዲያመች የቀረበ)
🖊 የእግዚአብሔርን ህላዌ/መለኮታዊ/የማይሸጋገሩ/የማይጋሩ (INCOMMUNICABLE)
ከፍጥረት ጋር የማይጋራቸው ናቸው።
እነዚህን ስናስብ እግዚአብሔርን ብቻ ነው የምናስበው። ለምሳሌ “ሁሉን ቻይነት”፣ “ሁሉን አዋቂነት”
🖊 የሚያጋራቸው/የሚያካፍላቸው (COMMUNICABLE)
ከፍጥረት ጋራ ባለው ግንኙነት የምናያቸው ናቸው፤ የሚያጋራቸው ናቸው።
የእግዚአብሔርን ባህርያት ሙሉ በሙሉ የምንካፈላቸውም አይደሉም፤ ሙሉ በሙሉ የማንካፈላቸውም አይደሉም።
4) ዓላማ
የእግዚአብሔርን ባሕርያት ማወቅ እግዚአብሔርን ለማወቅ ነው። ክብሩን ለማየት፣ ለማምለክ፣ ለመደነቅ፣ ለመገረም ነው።
ለጭቅጭቅ፣ ለመመራመር፣ ለመፈላሰፍ አይደሉም።
📍የእግዚአብሔር ባሕርያት (በተለይ የማይጋራቸው)
1) አይለወጤነት/ወጥነት (IMMUTABILITY)
እግዚአብሔር በማንነቱ፣ በሀሳቡ፣ በአላማው አይለወጥም፤ አይቀያየርም።
ነገሮች ሁሉ ቢለዋወጡም በማንነቱ እግዚአብሔር አይለወጥም፣ አቅጣጫ አይቀይርም።
በሰማይና በምድር እሱ ያለው ብቻ ይሆናል፤ እርሱ ግን አይለወጥም።
📖 መዝ 102:25-27
📖 ዕብ 1:11-12
📖 ያዕ 1:17
📖 ምሳ 19:21
📖 መዝ 33:1
📖 ኢሳ 46:9-11
ስንጸልይ አሳቡን ይመልሳል፤ እኛ ጸልየን እንቀበላለን። እኛ የምናሽከረክረው አምላክ የለንም።
“እግዚአብሔር ተጸጸተ” ሲል ያላሠበውን አደርገ ሳይሆን አቀባበሉ ይቀየራል፣ በሰው ቋንቋና በሰው ሁኔታ ይገለጣል እንጂ በማንነቱ አይቀየርም።
ስለ አንድ ነገር የተለያየ አቀባበል ሊኖረው ይችላል፤ በማንነቱ ግን አይቀየርም። ሰው እንዲገባው በሚችል መልኩ ይሠራል።
የእኛ ሁኔታ ሲለወጥ እሱም የተለወጠ ይመስለናል እርሱ ግን አይለወጥም።
2) አይወሰኔነት (INFINITE)
🖊 ከጊዜ አንጻር :- ዘላለማዊ (ETERNAL)
እግዚአብሔር በጊዜ አይወሰንም ዘላለማዊ ነው። ጅማሬም የለውም ፍጻሜም የለውም።
ጊዜን እራሱ ፈጥሮት እሱ ግን ከጊዜ ውስንነት ውጪ የሚኖር ነው
ዘመኑ መጀመሪያ እና መጨረሻ የለውም፤ እርሱ አልፋና ኦሜጋ ነው።
ያልተፈጠረ ሕያው ሆኖ የሚኖር እግዚአብሔር ብቻ ነው።
📖 ኢዮብ 36:26
📖 መዝ 90:2
እግዚአብሔር “ነበር” እና “ይሆናል” የለውም።
ከጊዜ ውጪ ነው ግን በጊዜ ውስጥ ይሰራል። ዘመን ይወስናል እንጂ እሱ ከዘመን ውጪ ነው።
የጀመረ ክብር የለውም የተገለጠ እንጂ።
🖊 ከስፍራ አንጻር፦ በሁሉ ቦታ መገኘት ((OMNIPRESENT)
በስፍራ አይወሰንም፤ በሁሉ ቦታ በአንድ ጊዜ አለ።
ስፍራ አይዝም ስፍራን
📖 ኤር 23:23-24
📖 መዝ 139:7-10
እግዚአብሔር በተለያየ ቦታ በተለያየ አላማ ይገኛል።
📖 አሞጽ 9:1-4
📖 ዕብ 1:3
3) ሁሉን አዋቂነት (OMNISCIENT)
እግዚአብሔር ሳይማር፣ መረጃ ሳይሰበስብ ሁሉን ያውቃል።
የትላንቱን፣ እየሆነ ያለውን፣ የሚሆነውን፣ ሊሆን የነበረውን ያውቃል።
📖 መዝ 147:4-5
📖 ማቴ 10:29-30
📖 ዕብ 4:13
የእግዚአብሔር ሁሉን አዋቂነት በጣም አስደሳች ነው፤ በጣምም አስፈሪ ነው።
📖 ኢሳ 40:27-30
📖 ዘፍ 17:1
ከብዙ ሰው የእግዚአብሔር ፍርሀት የራቀው እግዚአብሔርን ስላላወቅነው ነው።
እግዚአብሔር በሁሉ ቦታ አለ፤ በእግዚአብሔር ፊት ከኖርን ብንደክምም ብንዝልም በፊቱ እንሁን፤ እርሱ የማያየው ምንም ነገር የለም።
ሁኔታዎች ቢቀያየሩም እሱ አይቀያየርም፤ ያው ነው!