የጸጋ ስጦታዎች (ክፍል 2)

ትምህርተ መንፈስ ቅዱስ

Mamusha Fenta

Stream the sermon 

የጸጋ ስጦታዎች (ክፍል 2)

ትምህርተ መንፈስ ቅዱስ

Mamusha Fenta

ትምህርተ መንፈስ ቅዱስ

የጸጋ ስጦታዎች (ክፍል 2)

📌 በዚህ ትምህርት የጸጋ ስጦታዎችን በ2 እንከፍላቸዋለን

  • 1️⃣ መንፈስ ቅዱስ ለእያንዳንዱ አማኝ የሚሠጣቸው (1ቆሮ12-14) ብቃቶች፣ ስራዎች ናቸው
  • 2️⃣ የክርስቶስ ስጦታዎች ናቸው (ኤፌ 4:11) ሰዎች ናቸው

📌 በዚህ ሳምንት የመጀመሪያውን እንመልከት

  • የጸጋ ስጦታን በተመለከተ ሰጪው አምላክ ፍጹም ነው።
  • እግዚአብሔር የተሳሳተ ስጦታን አይሰጥም። ሰጪው ፍጹም ስለሆነ ስጦታዎቹም ፍጹማን ናቸው። ሰጪው ስህተት የለውም፤ ተቀባዩ ግን ፍጹም አይደለም።
  • ፍጸም ስጦታዎች ፍጹማን ባልሆኑ እቃዎች/ተቀባዮች ማለት ነው።
  • ፍጹም የሆኑ ስጦታዎች በደካማ እጆች ውስጥ ስለሚሆኑ አንዳንዴ ለተለየ አላማ ጥቅም ላይ ይውላሉ። ራስን ለማሳየት፣ ለንግድ ጥቅም ላይ ይውላሉ። በዚህ የተነሳ በጣም ብዙ ትርምስ አለ።
  • ሁለት ቃላትን እንመልከት

📌 አቅላይነት እና አጥላይነት

● አቅላይ

  • አንዳንድ ሰዎች እነዚህ ፍጹማን የሆኑ ስጦታዎች ፍጹማን ባልሆኑ ሰዎች ውስጥ ሲያዩ አቅላይ ይሆናሉ፣ የጸጋን ነገር ያቃልላሉ፣ ያክፋፋሉ፣ ቸል ይላሉ፣ አይጠሙም።
  • እግዚአብሔር የጸጋ ስጦታን የምር እንድንይዝ ይፈልጋል።
  • የጸጋ ስጦታ ትርፍ ትምህርት አይደለም፣ ጊዜ ከተረፈን የምናሰላስለው አይደለም። በጣም ልንጠማው የሚገባ ነው። ምክንያቱም ደግሞ ጌታን ተቀብለን ስንኖር እግዚአብሔር በጸጋ ስጦታ ጡንቻችንን ካላዳበረው እንዴት እንጨርሳለን? ከዘላለም ሕይወት መነጣጠል የለብንም።
  • እርግጥ ሰው የሚድነው በጸጋ ስጦታ አይደለም፣ ሰው ትንቢት ስለተናገረ ወይ ስለፈወሰ አይጸድቅም (ማቴ 7)
  • ትንቢት የተናገረ፣ ጋኔን ያወጣ ሁሉ መንግሥተ ሰማይ ይገባል ማለት አይደለም። ያ ማለት ግን አያስፈልግም ማለት አይደለም።
  • በጸጋ ያዳነን አምላክ በጸጋ ይደግፈንና በጸጋ ያቆመንና ያጸድቀናል።
  • በጸጋ ስጦታ ዙሪያ ስህተትም፣ ማሾፍም ስለበዛ፣ ሰውም ስላቀለለው እንዳይቀልብን! እግዚአብሔር ያከበደው ነውና እንጠንቀቅ።
    • 📖 1ተሰ 5:19
  • በጸጋ ስጦታ እያሾፍን እየዋልን በጸጋ ስጦታ የማገልገልን መታጠቅ እንታጠቃለን ብሎ ማሰብ አይቻልም። መቃወም አንድ ነው፤ ማሾፍ ሌላ ነገር ነው (ማቴ 12)።
  • ጸጋን ከሚያክፋፋ ጋራ ኀብረት አይኑራችሁ። ስናክፋፋ ውለን፣ ስናክፋፋ አድረን በጸጋ እንድንሞላ መጠበቅ አንችልም፤ ያራከስነውን አይሰጠንም።

● አጥላይ

  • የጸጋ ስጦታን ሁሉን የመቀበል ግዴታ የለብንም። ሰው በስሜቱም ብዙ ነገር ሊያደርግ ይችላል፤ ሰይጣንም አለ። ምክንያቱም ሰይጣን የጽድቅ አገልጋዮችን የመምሰል፣ የብርሀን መልአክ የመምሠል፣ ድንቅና ተአምራትን የማድረግ ችሎታ አለው።
    • 📖 1ተሰ 5:19-21….አታጥፉ..ሁሉን ፈትኑ መልካሙን ያዙ
  • የመንፈስ ቅዱስ ስራ በእግዚአብሔር ቃል የሚፈተሽ ነው፣ የሚመዘን ነው።
  • ስለዚህ የማያቃልል ግን የሚያጠል መሆን አለብን።
    • 📖 1ዮሐ 4:1

● ከማቅለልም ከማጥለልም በላይ መጠማት!

  • ማቅለልና ማጥለል መታዘብ ናቸው፤ ታዛቢ ግን እንድንሆን አልተጠራንም፤ የምንጠማ እንድንሆን ያስፈልገናል።
    • 📖 1ቆሮ 14:1
  • እግዚአብሔር ከአቅማችንና ከችሎታችን በላይ በጸጋ ስጦታዎች እንዲጠቀምብን መራብ፣ ያስፈልገናል።
  • የጸጋ ስጦታዎች ያሳድጋሉ፣ ያበስላሉ፣ ያንጻሉ።
  • በጣም ብዙዎቻችን ያለመብሰላችን ምክንያት ያለማገልገላችን ነው። ምክንያቱም የሚንቀሳቀስ ነገር ነው የሚያድገው፣ ቁጭ ያለ ነገር አያድግም።
  • በጸጋ ስጦታ ማገልገል ያንጸናል፣ ያነሳሳናል (ኤፌ 4:7)። ሁላችን አገልጋዮች ነን። ቤተክርስቲያን ሙሉ ናት። ምዕመኖቿ በጸጋ የታጠቁ ናቸው፤ መሪዎቿና አገልጋዮቿ ደግሞ አስታጣቂ ባለጸጋዎች ናቸው።
    • 📖 ኤፌ 4:12-13 …ሙሉ ሰው ወደመሆን…ፍጹማን እስክንሆን ዘንድ..

● የጸጋ ስጦታዎችን ዝርዝር (ብቃቶችን) በጥቂቱ እንመልከት

➥ የማይመስሉቱ:- የጸጋ ስጦታ መሆናቸውን የማናስተውላቸው፣ የማንጸልይባቸው

  • 📖 ሮሜ 12 …ማገልገል …
  • መምከር
  • ማገልገል
  • መለገስ
  • ማስተዳደር
  • ምህረት ማድረግ
  • የጸጋ ስጦታን የምንጠማው ለመድረክ አይሁን። መድረክ ላይ ያሉት የአካል ብልቶች በጣም ጥቂት ናቸው። ከመድረክ ጀርባ ያሉት ሲገለጡ ፊት ካሉት ይበልጣሉ።
  • የምናዳምቀውና የምንጸልየውም በመድረክ ላይ ላሉት ነው።
  • ቤተክርስቲያን መታመም የለባትም በጀርባ/በውስጥ ያሉትን ለማየት።
  • እግዚአብሔር ምን መክሊት ሰጥቶናል? ነው እንጂ ያልሆነውን እንድሆን እግዚአብሔር አልጠራንም። እግዚአብሔር የሚጠይቀን ለሰጠን ነገር ብቻ ነው።
  • በተሰጠን ማገልገል ትህትናን ይጠይቃል።

➥ ተአምራዊ የሆኑ (1ቆሮ 12 ያሉት ዘጠኙ)

  • በሶስት እንከፍላቸዋለን

1) የንግግር ስጦታዎች

  • ልሳን መናገር
  • በልሳን የተነገረውን መተርጎም
  • ትንቢት መናገር

2) የሀይል ስጦታዎች

  • ፈውስ
  • ተአምራትን ማድረግ
  • እምነት

3) የመገለጥ ስጦታዎች

  • ጥበብን መናገር
  • እውቀት መናገር
  • መናፍስትን መለየት

📌 የንግግር ስጦታዎች

  • የተለመዱ የስጦታ አይነቶች ናቸው
  • ለእያንዳንዳችን የሚሰጡ ስጦታዎች ናቸው
  • በጉባዬ ውስጥ የሚገለጡ ናቸው

● በልሳን የመናገር ስጦታ

  • ተናጋሪው በማያውቀው ቋንቋ የመናገር ብቃት ማለት ነው።
    • 📖 ሐዋ ስራ 2:
  • ልሳን መናገርን ድንቅ ያደረገው ያልተማሩ ሰዎች መናገራቸው ነው።
  • በዚህ ዘመን በልሳን የመናገር ስጦታ ይኑር አይኑር የሚያጠራጥረው ሁላችን በልሳን ስለምንናገር ነው።
  • በልሳን መናገር ለማያምኑ ምልከት ይሆናል (1ቆሮ 14:22)። ተናጋሪውን ያንጻል፣ በጉባኤ ሲተረጎም ደግሞ ጉባኤን ያንጻል 1ቆሮ 14:4)
  • በልሳን መጸለይ ከአይምሯችን ያወጣናል፣ ከምናውቀው ከውስን ቋንቋ ያወጣናል። ያላሰብነውን ያጸልየናል (1ቆሮ14:14-15)።

● በልሳን የተነገረውን የመተርጎም ስጦታ

  • ተአምር የሚያደርገው ነገር ተርጓሚውም አለማወቁ ነው
  • ልሳን የማይተረጎም ከሆነ ለእግዚአብሔር ነው የሚነገረው።
    • 📖 1ቆሮ 14:5፣ 13
  • በልሳን ለመናገር እንደምንጠማ ለመተርጎምም እንጠማ።

● ትንቢት መናገር

  • ትንቢት መናገር ማለት ነቢይ መሆን ማለት አይደለም።
  • ትንቢት ለእግዚአብሔር ልጆች በሙሉ የተሰጠ ነው።
  • ትንቢት እግዚአብሔርን ወክሎ መናገርና መስማት ማለት ነው።
  • ከእግዚአብሔር መስማት ደግሞ ለሁሉም የተሰጠ ነው። እግዚአብሔር የተናገረንን ለማጽናት ትንቢትን ያመጣል።
  • ሁላችን ሰሚዎች እንድንሆን የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆን፣ በመንፈስ እንድንጸልይ ተጠርተናል።
  • የትንቢት አላማ ሁልጊዜ የወደፊቱን መናገር አይደለም።
    • 📖 1ቆሮ 14:3 ያንጻል፣ ይመክራል፣ ያጽናናል

📌 የጸጋ ስጦታ ፍላጎት ያብዛልን!

  • በጸጋ ስጦታ የማገልገል እውነትና ድፍረት ተሰጥቶናል።
  • በጸጋ ስጦታ ለማገልገል አንድ ቀን ፍጹማን እስክትሆኑ አትጠብቁ።
    • 📖 1ጢሞ4:14 ማነሳሳት ይጠይቃል
  • ምንድነው የተሰጣችሁ የጸጋ ስጦታ? እሱን ለማወቅ እንጸልይ።

Share:

Recommended...

የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት 57

ማቴዎስ 12:15-21(አማ 54) ኢየሱስም አውቆ ከዚያ ፈቀቅ አለ። ብዙ ሰዎችም ተከተሉት፥ ሁሉንም ፈወሳቸው፥ እንዳይገልጡትም አዘዛቸው፤ በነቢዩ በኢሳይያስ የተባለው ይፈጸም ዘንድ እንዲህ ሲል፦ እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል። አይከራከርም አይጮህምም፥ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም። ፍርድን ድል ለመንሣት እስኪያወጣ፥ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም የሚጤስን የጥዋፍ...

Aberham Teklemariam

እነሆ ደስታችን ክፍል 2

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2 (አማ 54) በክርስቶስም አንዳች ምክር ቢሆን፥ የፍቅር መጽናናት ቢሆን፥ የመንፈስ ኅብረት ቢሆን፥ ምሕረትና ርኅራኄ ቢሆኑ፥ ደስታዬን ፈጽሙልኝ፤ በአንድ አሳብ ተስማሙ፥ አንድ ፍቅር አንድም ልብ አንድም አሳብ ይሁንላችሁ፤ ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን...

Nigussie Bulcha

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ትምህርት

NEW BIBLE STUDY SERIES (Intro) by Dr. Mamusha Fenta

...
Mamusha Fenta

Order Spiritual Maturity | A Book by Mamusha Fenta


Pickup location: Lighthouse Cafe, ACLA Church, Addis Ababa, Ethiopia

Filter by Preacher

Filter by Topic

Filter by Scripture

Filter by Resource Type

Resource Type

Filter by Series

Series