የቅዱሳት መጻሕፍት ቀኖና

ትምህርተ መፅሐፍ ቅዱስ ክፍል 3

Mamusha Fenta

Stream the sermon 

የቅዱሳት መጻሕፍት ቀኖና

ትምህርተ መፅሐፍ ቅዱስ ክፍል 3

Mamusha Fenta

የቅዱሳት መጻሕፍት ቀኖና (The Kanon of Scriptures)

እስካሁን ባለፉት ክፍሎች እንደተማርነው መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው፤ ከስህተት የጸዳ ነው፤ የበላያችን ነው ብለናል። ዛሬ ደግሞ የምናነሳው ጥያቄ የትኞቹ መጻሕፍት ናቸው እንደዚህ? በእግዚአብሔር ስም የተጻፈ መጽሐፍ ሁሉ እንደዚህ ነው ወይ? ብዙ መጻሕፍት ስለተጻፉ፥ ስለሚጻፉም ስለየትኞቹ መጻሕፍት ነው የምናወራው? በእግዚአብሔር ስም ስለተጻፉት መጻህፍት ነው ወይስ ሰዎች ዝም ብለው እግዚአብሔር ገልጦልኛል ብለው ስለጻፉት ነው? ከሁሉ መማር ይቻል ይሆናል፤ ሁሉን ግን ባለስልጣን ማድረግ አይቻልም።
📖 2ጢሞ 3:16-17

📍ትርጉም
ቀኖና (KANON):- የመጣበት የግሪክ ቃል ሲሆን መለኪያ ዘንግ/ ሕገ ደንብ/ሥርዓት/ልኬት/ ማለት ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት context፥ መጽሐፍ ቅዱስ ስለራሱ ሲናገር “መጽሐፍ” ይላል ፤ “መጽሐፍት” ይላል። በ”መጽሐፍ” ውስጥ “መጻሕፍት” አሉ።
“መጽሐፍ” Unified ማንነቱ ነው፤ ግን ደግሞ “መጻሕፍት” አሉ።
የትኞቹ “መጽሐፍት” ናቸው “መጽሐፍ” ውስጥ የሚገቡት? የሚለውን ነው ዛሬ የምናየው።
የተጻፈ ሁሉ መጽሐፍ አይባልም።
📖 ዮሐ 2:22 ….መጽሐፍ
📖 ዮሐ 5:39 ….መጻሕፍት
📖 ሉቃ 24:27….መጻሕፍት
እነዚህ መጻሕፍት በተለያዩ ክርስቲያን ማኀበረሰቦች ዘንድ የተለያዩ ቁጥሮች አሏቸው።
የመንፈስ ቅዱስ ምሪትና የእግዚአብሔር ቃልነት ሥልጣን ያሉባቸው የትኞቹ መጻሕፍት ናቸው?

📌 66ቱ?
እኛ የምናምነው 66ቱን ነው፤ (39 የብሉይ ኪዳንና 27 የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን የያዘው) በተለምዶ የፕሮቴስታንት ቀኖና ይባላል። እኛ የቆምነው እዚህ ላይ ነው።

📌 73ቱ?
የካቶሊክ ቀኖና ይባላሉ፤ 15 ተጨማሪ አፖክሪፋ (ድብቅ) መጻሕፍት ይባላሉ፤ አዋልድ (ተጨማሪ) መጻሕፍት ይባላሉ። 16ኛው ክፍለዘመን አካባቢ የተጨመሩ ናቸው። እነኚህ ተጨማሪ 15 መጻሕፍት አንድ ላይ ይነበቡ ነበር፤ እኩል ሥልጣን ግን አልሰጧቸውም ነበር፤ ቀስ ብለው ነው እኩል ሥልጣን የሰጧቸው።

📌 81ዱ?
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ጨምሮ ከ76-80 አሀዱ ይደርሳል።
66ቱ ላይ የትኛው ይውጣ የሚል ጭቅጭቅ የለም፤ የሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ነው።
እኛ እምነታችን 66ቱ የሁሉም አብያተ ክርስቲያናት መሠረት የሆኑት መጻሕፍት እነርሱ ብቻ ናቸው የእግዚአብሔር ቃላት የሚል ነው።

📍ለምን 66 ብቻ?
መጽሐፍ ቅዱስ ሁለት ክፍሎች አሉት፤ በሁለቱ ኪዳኖች የተከፈለ ነው።
📘 የብሉይ ኪዳን ቀኖና:-
39 (ከዘፍጥረት – ሚልኪያስ)
በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ናቸው።
የብሉይ ኪዳንን መጻሕፍት ተቀባይ የአይሁድ ሕዝብ ነው፤ ኪዳኑም ከእስራኤል ጀምሮ ለአለም ነው።
ስለዚህ ቅዱሳት መጻሕፍትን የተቀበለው ሕዝብ፤ አደራ የተሰጣቸው፤ የእግዚአብሔር ቃል ከእነሱ ወጣ የተባሉት ስንት መጻሕፍት ነበራቸው? የሚለውን ነው እኛ የምናየው።
የመጀመሪያውን ጽሑፍ (10ቱ ትዕዛዛት) የጻፈላቸው እግዚአብሔር ነው።
📖 ዘጸ 31:18
📖 ዘጸ 32:16
📖 ዘዳ 10:5 አቀማመጣቸው
እኚህኝን የመጀመሪያ ትዕዛዛት እግዚአብሔር በሰጠው በታቦቱ ውስጥ በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ነው የተቀመጡት። የጻፈውን በታቦቱ አስቀመጠው። እነዚህን ብቻ ሳይሆን ከዚያ በኋላ ሙሴ የጻፋቸውም አምስቱ ቶራ የምንላቸው የተቀመጡት በታቦቱ አጠገብ ነው።
እስከ ሚልኪያስ የትንቢት መጽሐፍ ድረስ የተጻፉትን መጻሕፍት በጥራዝ ሳይሆን በጥቅልሎች ነበር የሚያስቀምጧቸው። በ22 ጥቅልሎች የተጠቀለሉ መጻሕፍት ነበሯቸው። እነዚህ 22 ጥቅልሎች አሁን እኛ “ብሉይ ኪዳን” የምንላቸውን 39 መጻሕፍት የያዙ ናቸው።
📖 ሉቃ 4
ከሚልኪያስ ዘመን በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ታሪክ እንደሚያመለክተው አዲስ ኪዳን እስከሚከፈት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ 400 አመታት ነበሩ። እነኚህ 400 አመታት “400 የዝምታ አመታት” ይባላሉ።
በዚህ የዝምታ አመታት በተበተኑት አይሁድ ዘንድ በተለይም በግብፅ እስክንድርያ አካባቢ በነበሩ አይሁዳውያን ዘንድ የዚህ ዘመን ታሪኮችና እና መቃተቶች መጻፍ ጀመሩ። በተለይም ኢየሱስ ከመምጣቱ 200 አመታት በፊት ብዙ መጽሐፎች ተጻፉ። የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ጌታችን ከመምጣቱ 200 አመት በፊት በግሪክ ቋንቋ ተተረጎመ “የሰብአ ሊቃናት ትርጉም” ይባል ነበር። እሱ ሲተረጎም አንዳንዶቹ፥ እነኚያ በ400ው የዝምታ አመታት የተጻፉትም አብረው መተርጎም ጀመሩ። አብዛኞቹ ተጨማሪ መጻሕፍት የተጻፉት በግሪክ ቋንቋ ነበር፤ በአብዛኛው የተሰራጩትም በግብጽ ነው። እነኚህ ሲጻፉ በድብቅ ስለሆነና በግሪክም ስለተጻፉ አፖክሪፋ ተባሉ።
አይሁድ እንዴት ያዩአቸው ነበር? ካልን ያነቧቸው ነበር በምንም አይነት ግን ከ39ኙ ጋር አስጠግተዋቸው አያውቁም ነበር። “መጻሕፍት” ሲሉ ያስጠጓቸው ነበር፤ “መጽሐፍ አድርገው ግን ያነቧቸዋል። የእግዚአብሔር ቃላት አድርገው አያዩአቸውም በብዛት ግን ይሠራጩ ነበር።

📌 ኢየሱስና ሐዋርያቱ እነኚህን መጻሕፍት እንዴት ያዩአቸው ነበር? 39ኙን ብቻ ነው የእግዚአብሔር ቃል (Scripture) የሚሏቸው። ጌታ ኢየሱስም ሆነ ሐዋሪያቱ የትምህርታቸው የሥልጣን ምንጭ፤ እንደ ቅዱሳት መጻሐፍት የሚሏቸው የአይሁድን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን ነው። ሕጉ፤ ነቢያቱ፤ መጻሕፍቱ፣ መዝሙራት ይሏቸው ነበር።
📖 ማቴ 5:17
📖 ሉቃ 24:44
እኛም የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ላይ የማንጨምረው ኢየሱስ እና ሐዋሪያቱ ስላልጨመሩ ነው።
📖 2ጢሞ 3:15-17
ኢየሱስ እነኚን መጻሕፍት መቀበሉ ብቻ ሳይሆን ሌሎቹን በዝምታው ጊዜ የተጻፉትን አላነሳም አልተቀበለም።
📖 ማቴ 23:35-36 — 2ኛ ዜና 24:20-21
📘 አዲስ ኪዳን ቀኖና:-
27 (ከማቴዎስ – የዮሐንስ ራዕይ)
ለምንድነው 27ቱ ላይ የቆምነው? ሐዋሪያቱ ከመሞታቸው በፊት የአዲስ ኪዳንን አብዛኞቹን መጻሕፍት እንደ Scripture ማየት ጀምረው ስለነበረ ነው። የመጀመሪያዎቹ ጸሐፍት/ሐዋርያት የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን፤ ወንጌላትንና መልእክታትን በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር በሰጠበት በዚያ ሥልጣን ማየት ጀምረው ስለነበረ ነው።
📖 2ጴጥ 3:15-16
📖 1ጢሞ 5:17-18

📌 ሐዋሪያዊነት
በቀጥታ በሐዋርያት የተጻፉ በመሆናቸውና ከሐዋርያት ትምህርት ጋራ ስሙሙ የሆኑ ትምህርቶችን በማስተማራቸው።

📌 የቤተክርስቲያን እና የቤተክርስቲያን ጉባኤዎች ሚና
🖊 ቀኖናን በተመለከተ የእግዚአብሔር ቃል መሆናቸውን እውቅና መስጠት ነው እንጂ የእግዚአብሔር ቃል ማድረግ አይደለም። የቤተክርስቲያን ሥልጣን አይደለም መጽሐፍ ቅዱስን የእግዚአብሔር ቃል ያደረገው።
የቤተክርስቲያን ሥልጣን ከእግዚአብሔር ቃል ሥልጣን በላይ ነው ብለን አናምንም።
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር ቃል የምትመራ ናት እንጂ የእግዚአብሔር ቃል ፈጣሪ አይደለችም። የእግዚአብሔር ቃል ለዪ፣ የእግዚአብሔር ቃል ጠባቂ፣ የእግዚአብሔር ቃል ሞግዚት፣ የእግዚአብሔር ቃል አሳታሚ፣ የእግዚአብሔር ቃል አሠራጭ፣ የእግዚአብሔር ቃል ሰባኪ፣ የእግዚአብሔር ቃል ተናጋሪ እንጂ ፈጣሪ አይደለችም፤ ፈጣሪው መንፈስ ቅዱስ ነው።

  • የመጽሐፍ ቅዱስን ቀኖና በተመለከተ ትልልቅ ጉባኤዎች አልተካሔዱም።
    🖊 ምስራቃዊያን አብያተ ክርስቲያናት 367 ዐ.ም ከክርስቶስ ልደት በኋላ
  • ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዱስ አትናቲዎስ በጻፈው 39ኛው መልእክቱ የመጽሐፍትን ዝርዝር (66ቱን ብቻ) አስቀመጠ።
    🖊 ምዕራባውያን ከ30 አመት በኋላ በ397 0.ም በካርቲጅ ጉባኤ ተወያዩና እነኚህ መጽሐፍት የቀኖና አካል መሆናቸውን ተቀበሉ።
  • ትልልቅ ጉባዔዎች ባይካሔዱም በእነኚህ ጉባኤዎች 66ቱን መጻሕፍት ሁለቱም ተቀበሏቸው።
    📌 የአፖክሪፋ/ የአዋልድ መጽሐፍ ጉዳይስ?
  • ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠጋግተው የተጻፉበት መጽሐፍ፤ ጄሮም የተባለ ተርጓሚ 400 ዐ.ም የአይሁድን ሲተረጉም አብሮ ተርጉሟቸዋል።
  • እንደ እግዚአብሔር ቃል ሳይሆን እንደ ቤተክርስቲያን መጻሕፍት ወይም ተጨማሪ መጻሕፍት፤ ተጨማሪ ቀኖና እየተባሉ መውጣት ጀመሩ፤ እኩል ግን ስልጣን የላቸውም ነበር።
  • እኛ እነኚህን የማንቀበልበት ምክንያት
    📍ራሳቸውም የእግዚአብሔር ቃላት ነን ብለው አይመሠክሩም።
    📍 የአይሁድ ቀኖና አይቀበላቸውም
    📍 ኢየሱስና ሐዋርያቱ አይቀበሏቸውም
  • ነገር ግን በሕዝብ ዘንድ የታወቁ ታሪኮች ስለሆኑ አንዳንዶቹን ተጽፈው እናገኛቸዋለን።
    📖 ይሁዳ 14:15 (ቁ.9)
  • መጠቀስ ብቻውን እኩል ስልጣን አያሰጥም። የተጠቀሰ ሁሉ የእግዚአብሔር ቃል አይደለም።
    📖 ቲቶ 1:12
    📖 ሐዋ ስራ 27:28
    📍የትምህርት ተቃርኖም አላቸው
    📌 ከዚህ በኋላስ ቢገኝ ቀኖና ክፍት ነው ወይስ ዝግ ነው መሆን ያለበት?
    🖊 ቀኖና ዝግ ነው ብለን እናምናለን፤ ለምን?
    1) የመጨረሻውን መገለጥ እግዚአብሔር ሰጥቶናል ብለን እናምናለን እሱም ኢየሱስ ነው፤ አሁን የምንጠብቀው የመንግሥቱን መገለጥ ነው እንጂ መንግሥቱማ መጥቷል
    2) የመጨረሻው የኢየሱስ መገለጥ ሲጻፍ በራዕይ 22:18-19 ዘግቶታል።
  • ክርስቶስን ለማመን፣ ለመዳን፣ ዳግም ለመወለድ፣ እግዚአብሔርን ለማወቅ መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ ነው።

🖊መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፈ፣ ትክክለኛና ከስህተት የጸዳ፣ በውስጡም ስድሳ ስድስት ቅዱሳት መጻሕፍትን በአንድነት የያዘ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን እናምናለን።

Share:

Recommended...

ኤፌሶን ትምህርት 16

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3:1–13 (አማ54) ስለዚህም አሕዛብ ስለ ሆናችሁ ስለ እናንተ የክርስቶስ ኢየሱስ እስር የሆንሁ እኔ ጳውሎስ ለእግዚአብሔር እንበረከካለሁ። ለእናንተ ስለ ተሰጠኝ ስለ እግዚአብሔር ጸጋ መጋቢነት በእርግጥ ሰምታችኋል፤ አስቀድሜ በአጭሩ እንደ ጻፍሁ፥ ይህን ምሥጢር በመግለጥ አስታወቀኝ፤ ይህንም ስታነቡ የክርስቶስን ምሥጢር እንዴት እንደማስተውል ልትመለከቱ ትችላላችሁ፤ ይህም፥ አሕዛብ አብረው እንዲወርሱ፥ በአንድ አካልም...

Aberham Teklemariam

የዮሐንስ ወንጌል ትምህርት 28

“Hiwot Tegelete” John Chapter 8: Part 3 by Mamusha Fenta

...
Mamusha Fenta

ኤፌሶን ትምህርት 54

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6:13–17 (አማ54) ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ። – እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤ በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ...

Mamusha Fenta

Order Spiritual Maturity | A Book by Mamusha Fenta


Pickup location: Lighthouse Cafe, ACLA Church, Addis Ababa, Ethiopia

Filter by Preacher

Filter by Topic

Filter by Scripture

Filter by Resource Type

Resource Type

Filter by Series

Series