የንጉሡ ሥልጣን

የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት 39

Mamusha Fenta

የንጉሡ ሥልጣን

የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት 39

Mamusha Fenta
Topics: Faith, Men, Suffering, War

ማቴ 8፡1-17 (አማ54)
ከተራራም በወረደ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት። እነሆም፥ ለምጻም ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ እያለ ሰገደለት። እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና። እወዳለሁ፥ ንጻ አለው። ወዲያውም ለምጹ ነጻ። ኢየሱስም። ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፥ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፥ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ሙሴ ያዘዘውን መባ አቅርብ አለው። ወደ ቅፍርናሆምም በገባ ጊዜ የመቶ አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ብላቴናዬ ሽባ ሆኖ እጅግ እየተሣቀየ በቤት ተኝቶአል ብሎ ለመነው። ኢየሱስም። እኔ መጥቼ እፈውሰዋለሁ አለው። የመቶ አለቃውም መልሶ። ጌታ ሆይ፥ በቤቴ ጣራ ከታች ልትገባ አይገባኝም፤ ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር፥ ብላቴናዬም ይፈወሳል። እኔ ደግሞ ለሌሎች ተገዥ ነኝና፥ ከእኔም በታች ጭፍራ አለኝ፤ አንዱንም። ሂድ ብለው ይሄዳል፥ ሌላውንም። ና ብለው ይመጣል፥ ባሪያዬንም። ይህን አድርግ ብለው ያደርጋል አለው። ኢየሱስም ሰምቶ ተደነቀና ለተከተሉት እንዲህ አለ። እውነት እላችኋለሁ፥ በእስራኤል እንኳ እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም። እላችኋለሁም፥ ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር በመንግሥተ ሰማያት ይቀመጣሉ፤ የመንግሥት ልጆች ግን በውጭ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል። ኢየሱስም ለመቶ አለቃ። ሂድና እንዳመንህ ይሁንልህ አለው። ብላቴናውም በዚያች ሰዓት ተፈወሰ። ኢየሱስም ወደ ጴጥሮስ ቤት ገብቶ አማቱን በንዳድ ታማ ተኝታ አያት፤ እጅዋንም ዳሰሰ፥ ንዳዱም ለቀቃት፤ ተነሥታም አገለገለቻቸው።
በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደረባቸውን ብዙዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ በነቢዩ በኢሳይያስ። እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ መናፍስትን በቃሉ አወጣ፥ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ።

Matthew 8:1-17

When he came down from the mountain, great crowds followed him. And behold, a leper came to him and knelt before him, saying, “Lord, if you will, you can make me clean.” And Jesus stretched out his hand and touched him, saying, “I will; be clean.” And immediately his leprosy was cleansed. And Jesus said to him, “See that you say nothing to anyone, but go, show yourself to the priest and offer the gift that Moses commanded, for a proof to them.” When he had entered Capernaum, a centurion came forward to him, appealing to him, “Lord, my servant is lying paralyzed at home, suffering terribly.” And he said to him, “I will come and heal him.” But the centurion replied, “Lord, I am not worthy to have you come under my roof, but only say the word, and my servant will be healed. For I too am a man under authority, with soldiers under me. And I say to one, ‘Go,’ and he goes, and to another, ‘Come,’ and he comes, and to my servant, ‘Do this,’ and he does it.” When Jesus heard this, he marveled and said to those who followed him, “Truly, I tell you, with no one in Israel have I found such faith. I tell you, many will come from east and west and recline at table with Abraham, Isaac, and Jacob in the kingdom of heaven, while the sons of the kingdom will be thrown into the outer darkness. In that place there will be weeping and gnashing of teeth.” And to the centurion Jesus said, “Go; let it be done for you as you have believed.” And the servant was healed at that very moment. And when Jesus entered Peter’s house, he saw his mother-in-law lying sick with a fever. He touched her hand, and the fever left her, and she rose and began to serve him. That evening they brought to him many who were oppressed by demons, and he cast out the spirits with a word and healed all who were sick. This was to fulfill what was spoken by the prophet Isaiah: “He took our illnesses and bore our diseases.”

Share:

Recommended...

የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት 119

ኢየሱስን የያዙትም ጻፎችና ሽማግሎች ወደ ተከማቹበት ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ወሰዱት። ጴጥሮስ ግን እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ ሩቅ ሆኖ ተከተለው፥ የነገሩንም ፍጻሜ ያይ ዘንድ ወደ ውስጥ ገብቶ ከሎሌዎቹ ጋር ተቀመጠ። የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ሸንጐውም ሁሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ላይ የሐሰት ምስክር ይፈልጉ ነበር፥ አላገኙም፤ ብዙም የሐሰት ምስክሮች ምንም ቢቀርቡ...

Mamusha Fenta

1ኛ ዮሐንስ ትምህርት አከፋፈል

1ኛ ዮሐንስ መልእክት የመጽሃፉ የጥናት አከፋፈል በማሙሻ ፈንታ 1 John Bible Study Divisions by Mamusha Fenta

...
Mamusha Fenta

የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት 104

የማቴዎስ ወንጌል 23:37-24:2 (አማ54) ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም። እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል። እላችኋለሁና፥ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም። ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት...

Mamusha Fenta

Order Spiritual Maturity | A Book by Mamusha Fenta


Pickup location: Lighthouse Cafe, ACLA Church, Addis Ababa, Ethiopia

Filter by Preacher

Filter by Topic

Filter by Scripture

Filter by Resource Type

Resource Type

Filter by Series

Series