የእግዚአብሔር ቃል

ትምህርተ መፅሐፍ ቅዱስ ክፍል 1

Mamusha Fenta

Stream the sermon 

የእግዚአብሔር ቃል

ትምህርተ መፅሐፍ ቅዱስ ክፍል 1

Mamusha Fenta

Doctrine of Scriptures

📍መጽሐፍ ቅዱስ (Bibliology :- Bibilo+logy ; የመጽሐፍት ጥናት)
1) ሥልጣን (AUTHORITY)
2) መገለጥ (REREVELATION)
3) እስትንፋሰ መለኮት (INSPIRATION)

  • በጥንት የእግዚአብሔር ሕዝብ “የመጽሐፉ ሕዝብ” ይባል ነበር።
  • እኛ የመጽሐፉ ሕዝብ ነን እንጂ የመጽሐፉ ጸሐፊ አይደለንም።
  • የቃሉ ምንጭ ቤተ ክርስቲያን አይደለችም፤ የቃሉ ጠባቂ እንጂ።
  • መጽሐፍ ቅዱስን እንደፈለግን እንድንተረጉመው አልተሰጠንም።
  • የአንድን ዘመን ክርስትና በመጽሐፉ አያያዝ መገምገም እንችላለን።
    📖 2 ጴጥ 1:16-21
    📖 2 ጢሞ 3:16-17

❶) ሥልጣን (AUTHORITY)
መጽሐፍ ቅዱስ የመጨረሻው ባለሥልጣን (ቱምቢ)📖 አሞጽ 7:7-8…ቱምቢ…ነው። መመሪያችን (MANUAL) መጽሐፍ ቅዱስ ነው። መስመራችንን፣ አስተምህሯችንን፣ እውነቱን ከውሸት የሚለይልን መጽሐፍ ቅዱስ ነው።
📍 የሥልጣን መሠረቶች፦
ግራውን ከቀኝ የምንለካበት
የምግባር፣ የአኗኗር፣ የአስተሳሰብ መለኪያ
📎 ለአንዳንድ ሰዎች ባለሥልጣናቸው/ቱምቢያቸው/ መለኪያቸው፦
📌 አመክንዮ (REASON):- የሰው አስተሳሰብ (አዕምሮ)
📖 መሳ 21:25
📖 2 ቆሮ 4:4
📖 1ቆሮ 2:14
“አዕምሮዬ የደረሰበት ነገር ነው መለኪያዬ፣
አዕምሮዬ ልክ ነው ያለኝ ልክ ነው፤ ልክ አይደለም ያለኝ ልክ አይደለም” የሚሉ
ክርስትና ከአመክንዮ ውጪ አይደለም፤ ነገር ግን መደገፊያችን/መለኪያችን ሊሆን አይችልም፤ ምክንያቱም አዕምሯችን እግዚአብሔርን በመለከተ አይታመንም፤ ለኀጢአት ያዳላል። እግዚአብሔርን ሙሉ በሙሉ ሊያሳየን አይችልም።
አመክንዮ ብቻውን የሥልጣን መሠረት ሊሆን አይችልም።
📌 ልምምድ (EXPERIENCE)
“ስለማመደው የሠራ የመሠለኝ እውነት ነው፤ የሠራ ያልመሠለኝ ደግሞ እውነት አይደለም” የሚሉ
“ደስ ስላለኝ፣ የተሠማኝ የእግዚአብሔር ሀሳብ ነው” የሚሉ
መለኪያቸው “Feel Good” የሆነ
ስንለማመደው ጥሩ የሆነ ነገር ሁሉ ከእግዚአብሔር ላይሆን ይችላል።
📌 ባለ ሥልጣን (መሪዎች/ቅቡዐን)
“እነሱ ልክ ነው ያሉት ልክ ነው፣ ልክ አይደለም ያሉት ልክ አይደለም” የሚሉ
የሥልጣናቸው መለኪያ ሰዎች ናቸው
እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን መሪዎች የሰጠው ሥልጣን አለ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል የማስፈጸም ሥልጣን እንጂ የራሳቸውን ሥልጣን አይደለም። መሪው ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ሲጣላ ተሳስቷል።
📌 ባሕል/ትውፊት (TRADITION)
ባሕል:- ሰዎች የፈጠሩት የአኗኗር ዘይቤ/ዘዴ ነው።
እግዚአብሔር ባሕል ጠል አይደለም። ክርስቲያናዊ ባሕል ግን የለም።
የራሱ ጉዳትና ጥቅም አለው። ፍጹም የሆነ ባሕል የለም፤ ሙሉ በሙሉ መጥፎ የሆነም ባሕል የለም። ምክንያቱም ባሕል ሰው ሰራሽ ነው።
የፈለገ ዘመን ቢኖሩም መልካም ያለሆነው መልካም አይደለም፤ መልካም የሆነው መልካም ነው።
በአንድ ባሕል ውስጥ እውነት ካለች ለረጅም ጊዜ ስትኖርም እውነት ናት፤ መርዘምና ማጠር አይቀይራትም። ውሸትም እንደዛው።
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሕል አለ። ባሕል ጠል አንሁን። ግን የእውነት መለኪያ/ባለሥልጣን ሊሆን አይችልም።
📖 ማቴ 15:3
ባሕል/ወግ ከእግዚአብሔር ቃል ሲጣላ እንጥለዋለን።
📎 ሦስቱም አያስፈልጉም እያልን አይደለም፤ እስከመጨረሻው ግን የእውነት መለኪያ/ባለሥልጣናችን ሊሆኑ አይችሉም እያልን ነው። እንከን አልባ የሕይወታችን መለኪያ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።
📎 ለምን? በማንነቱ ምክንያት!


❷) መገለጥ (REREVELATION)
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር መገለጥ ነው።
ሰው እግዚአብሔርን ለማወቅ የመገለጥ ጥገኛ ነው። እግዚአብሔር በአዕምሮ አይደረሥበትም።
📖 1ጢሞ 1:17
📖 ኢዮ 36:26
📖 ኢሳ 55:8-10።
ራሱን ያልሠወረ አምላክ ነው የምናመልከው።
መገለጥ እግዚአብሔርን እንድናውቀው፣ እንድንከተለው የሠጠን ራሱን የገለጠበት መንገድ ነው።
መገለጥ ‘ክዳን ማንሳት፣ መጋረጃ መግለጥ’ ነው። መገለጥ አዲስ ነገር አያመጣም። ሲገለጥልን “እንደዚህ ሆነ” ሳይሆን “በራልኝ” ነው የምንለው።
📍መጽሐፍ ቅዱሳዊ መገለጦች
1) አጠቃላይ/ጥቅል መገለጦች
ለሁሉ ሰው በሁሉ ቦታ ያለ መገለጥ!
ስለ እግዚአብሔር መረጃ የሚሰጥ መገለጥ!
ይህንን መገለጥ ለማግኘት ቤተ ክርስቲያን መምጣት፣ የኃይማኖት ሰው ማግኘት የለብንም።
ምሳሌ :- ፍጥረታት
የእምነት መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ፍጥረትን አይቶ ወደ ፈጣሪው ሊመጣ ይችላል፣ መልካም ሥነምግባርን ለማዳበር ለመገንባት ይችላሉ።
📖 መዝ 19:1-6
📖 ሮሜ 1:18-21
📖 ሮሜ 2:14-16
2) ልዩ መገለጥ
ለተቀበለው ሰው ድነትን የሚሠጥ ነው።
የተወሰኑ ሰዎች የሚያገኙት መገለጥ፣ ወደ እግዚአብሔር የሚያመጣ መገለጥ ነው።
“ቃል” ልንለው እንችላለን፤ እግዚአብሔር በተለያየ መንገድ ተገልጧል፤ እግዚአብሔር ከጥንት በሁለት አይነት ቃል ተገልጧል፤ ‘ሰው በሆነው ቃል’ እና ‘በተጻፈው ቃል’
ክርስቶስ የእግዚአብሔር መገለጥ
የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔር መገለጥ
📖 ዕብ 1:1-2
📖 ዮሐ 1:1 /14:18
📎 በምን መልኩ ነው ይሔ መገለጥ የመጣው?
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር መገለጥ የሆነበት መንገድ; በመንፈስ ቅዱስ ተአምር በሰው በኩል ሰው እንደሆነው እንደቀደመው መገለጥ፤ በመንፈስ ቅዱስ ተአምር በሰዎች በኩል አልፎ የእግዚአብሔር ሃሳብ የተገለጠበት የእግዚአብሔር ንግግር ሆነ። ስለዚህ ምን እንለዋለን?


❸) እስትንፋሰ መለኮት (INSPIRATION)
📖 2 ጴጥ 1:21
📖 2 ጢሞ 3:16-17
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር እስትንፋስ ማለት ነው።
📖 2ጴጥ- 3:1-2
የእግዚአብሔር እስትንፋስ እየመራቸው ቅዱሳን ሰዎች የጻፉት ነው። ምንጩ ሰው አይደለም፤ የሰዎቹ ቋንቋና ሁኔታ ውስጡ አለ።
መንፈስ ቅዱስ በጸሐፊዎቹ personality፣ ቋንቋ፣ ሁኔታ አልፎ የሰጠን የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ እሱ የሥልጣን መለኪያችን ነው።


🏷 ማጠቃለያ:- መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፈ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን እናምናለን!

Share:

Recommended...

1ኛ ቆሮንቶስ ትምህርት 25

Meskelun Menor by Mamusha Fenta on 1 Corinthians – Chapter 7 – Part 7 “መስቀሉን መኖር” 1ኛ ቆሮንቶስ : ምዕራፍ 7 – ክፍል 7 በማሙሻ ፈንታ

...
Mamusha Fenta

የዮሐንስ ወንጌል ትምህርት 24

Mamusha Fenta

የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት 36

ማቴ 7:15-20 (አማ54)የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል። መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም። መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ...

Mamusha Fenta

Order Spiritual Maturity | A Book by Mamusha Fenta


Pickup location: Lighthouse Cafe, ACLA Church, Addis Ababa, Ethiopia

Filter by Preacher

Filter by Topic

Filter by Scripture

Filter by Resource Type

Resource Type

Filter by Series

Series