ማቴ 15:10-20 (አማ54)
“ሕዝቡንም ጠርቶ፦ ስሙ አስተውሉም፤ ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፥ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው አላቸው። በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው፦ ፈሪሳውያን ይህን ቃል ሰምተው እንደ ተሰናከሉ አወቅህን? አሉት። እርሱ ግን መልሶ፦ የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል። ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ አለ። ጴጥሮስም መልሶ፦ ምሳሌውን ተርጕምልን አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ እናንተ ደግሞ እስካሁን የማታስተውሉ ናችሁን? ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል አትመለከቱምን? ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፥ ሰውንም የሚያረክሰው ያ ነው። ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና። ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው እንጂ፥ ባልታጠበ እጅ መብላትስ ሰውን አያረክሰውም።”
Matthew 15:10-20 (ESV)
“And he called the people to him and said to them, “Hear and understand: it is not what goes into the mouth that defiles a person, but what comes out of the mouth; this defiles a person.” Then the disciples came and said to him, “Do you know that the Pharisees were offended when they heard this saying?” He answered, “Every plant that my heavenly Father has not planted will be rooted up. Let them alone; they are blind guides. And if the blind lead the blind, both will fall into a pit.” But Peter said to him, “Explain the parable to us.” And he said, “Are you also still without understanding? Do you not see that whatever goes into the mouth passes into the stomach and is expelled? But what comes out of the mouth proceeds from the heart, and this defiles a person. For out of the heart come evil thoughts, murder, adultery, sexual immorality, theft, false witness, slander. These are what defile a person. But to eat with unwashed hands does not defile anyone.””