ትምህርተ ሥላሴ (ክፍል 1)
የሥላሴ ትምህርት ለክርስትና አስተምህሮ ዋና እምብርት ነው። የክርስትናን እምነት ከሌሎቹ ኃይማኖቶች ለየት የሚያደርገው የሥላሴ ትምህርት ነው። ኃይማኖቶችን በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፦
🖊ብዝሀ አማልክት- ብዙ አማልክት ያሏቸው (ፖለቲየስቲክ)
- ቡድሒዝም
🖊 አሀዳዊ የሆኑ / አሀዱአዊ – አንድ አምላክ የሚያመልኩ (ሞኖቲየስቲክ)
- ይሁዲነት
- ክርስትና
- እስልምና
ክርስትና ሞኖቲየስቲክ ቢሆንም ከሌሎቹ ኃይማኖቶች ግን የሚለይ ነው። የሚለይበትም ምክንያት አሀዱ አምላክ ግን በስሉስነት /ሥላሴን በማመን የሚለይ ነው። ሌሎቹ ግን በዚህ አያምኑም።
የሥላሴ ትምህርት ለመረዳትና ለማስረዳት የሚከብድ ትምህርት ነው። አንዳንዶቹ እምነቶች ክርስቲያኖች ሦስት አማልክት እንደምናመልክ ያስባሉ። ክርስትና ሦስት አማልክት የሉትም፤ አንድ አምላክ ነው ያለው።
አንዳንድ ፍልስፍላ ውስጥ ያሉ ደግሞ ‘ሥላሴ’ የሚል ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም ብለው ይከራከራሉ። ‘ሥላሴ’ የሚለው ቃል መማሪያ ቴክኒካችን እንጂ ቃሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። ሥላሴ ዶክሪኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ቃሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባይገኝም ሀሳቡ ግን ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ አለ።
አሀዱ ስሉስ፥ እግዚአብሔር አንድ አምላክ ነው፤ ሦስትነት ግን አለው።
ሙሉ በሙሉ እንዳንረዳው ከባድ ነው፤ ስለከበደን እንዳንተወው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አለ። ስለዚህ በትክክል ማወቅና በቻልነው መጠን ማብራራትን ይጠይቃል።
እግዚአብሔር ራሱን በስሉስነት ገልጧል። ስለዚህ እግዚአብሔርን ለማወቅ፣ ለድነት፣ ለማምለክ የሥላሴ ትምህርትን ማወቅ አለብን።
ድነት
- መዳንን እንዴት ነው የምንገልጠው? መዳን ከሥላሴ ጋር የተያያዘ ነው። 📖 ኤፌ 1:
- የአብ የመምረጥ ፍቅር፣ የወልድ የቤዛነትና የመሰጠት ፍቅር፣ የመንፈስ ቅዱስ በውስጣችን መኖር መዳን ይሔ ነው። 📖 1ጴጥ 1:1-2
- እግዚአብሔር አብ እንዳወቀን፣ በክርስቶስ ደም እንደተረጨን፣ በመንፈስ ቅዱስ እንደተቀደስን ማመን ነው መዳን። 📖 ማቴ 28:10
- ሰው ደቀ መዝሙር እንዴት ይሆናል? ሥሉስ የሆነውን አምላክ አምኖ በመጠመቅ።
- የምናመልከው ትክክለኛ አምላክ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፤ አምልኮ ከሥላሴ ጋር የተያያዘ ነው። እውነተኛው አምላክ አንድ አምላክ በሥሉስነት የተገለጠው ነው። 📖 ራዕ 4-5
- ሦስት አማልክት አናመልክም አንዱ አምላክ ግን በሥሉስነት ነው የተገለጠው። 📖 ኢሳ 11:
🖊 ትምህርተ ሥላሴን በተመለከተ፥
የእግዚአብሔር አንድነት (ONENESS)
- አንድ አምላክ ብቻ አለ! ነው እምነታችን።
- እግዚአብሔር በባሕሪ፣ በመለኮት፣ በህላዌው፣ በመለኮትነት አንድ ነው! ሌላ የለም፣ አንድ አምላክ እናመልካለን።
- 📖 ዘጸ 20:2-3
- 📖 ዘዳ 4:35
- 📖 ዘዳ 6:4-5
- 📖 ኢሳ 45:10
- 📖 ኢሳ 43:10
- 📖 1ቆሮ 8:4-6
- 📖 1ጢሞ 1:17
- 📖 ይሁ 1:25
- የሥላሴ አማኞች አንድ አምላክ እናመልካለን።
- በባህሪ፣ በመለኮት፣ በማንነት፣ በህላዌ አንድ፤ በአካል ግን ሦስት!
የእግዚአብሔር ሦስት አካልነት (THREE-NESS)
- እግዚአብሔር በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስትነት አለው። One God, three persons.
1) እግዚአብሔር አብ
- ፍጹም አምላክ ነው!
- አምላክ ነው ስንል አብ ሲደመር እግዚአብሔር ወልድ ሲደመር እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ይሆናል አንድ አምላክ ማለት አይደለም። እግዚአብሔር አብ በራሱ፣ እግዚአብሔር ወልድ በራሱ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም በራሱ አምላክ ነው።
- መጽሐፍ ቅዱስ ‘አባት’ እያለ የሚጠራው እግዚአብሔር አብን ነው። ‘እውነተኛ አምላክ’ን ለአብም ለወልድም ተጠቅሟል።
- 📖 ዮሐ 17:3
- 📖 1ቆሮ 8:6
- 📖 ኤፌ 1:3
2) እግዚአብሔር ወልድ (በትምህርተ ክርስቶስ በሰፊው እንመለስበታለን)
- ብቻውን አምላክ ነው።
- 📖 ዮሐ 1:1
- በእግዚአብሔር ዘንድ ያለ እግዚአብሔር ያደርገዋል።
- 📖 ዮሐ 1:18
- 📖 ዮሐ 20:28
- 📖 ሮሜ 9:5
- በስጋ የመጣ ግን ለዘላለም የተባረከ።
- 📖 1ዮሐ 5:20
3) እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ
- የሚመራ፣ የሚያስተምር፣ ከአብና ከወልድ ጋር እኩል የሚጠራ፣ የሚመለክ።
- 📖 ሐ. ሥራ 5:3-4
- 📖 2ቆሮ 3:17-18
- አብ ወልድ አይደለም፣ ወልድም መንፈስ ቅዱስ አይደለም።
ሦስትነት በአንድነት (THREE-IN-ONENESS)
- አሀዱ ሥሉስነት!
- የሥላሴ አስተምህሮ የጀመረ አይደለም፤ እግዚአብሔር ለዘላለም ሥሉስ ነው። ሥሉስ ያልሆነበት ዘመን የለም።
- በእግዚአብሔር አንድነት ውስጥ ሦስትነት አለ። ይሔ በብሉይም በአዲስ ኪዳንም የምናገኘው አስተምህሮ ነው።
1) ብሉይ ኪዳን
- ውሱን መገለጥ ነው፤ ሙሉ አይደለም፤ ጥላ ነው።
- መገለጥ progressive ነው። ቀስ በቀስ እየጨመረ የተሰጠን ነው፤ መቼም አንደርስበትም።
- አንዳንዶች “እግዚአብሔር ራሱን በብዙ ቁጥር “እኛ” እያለ ያወራው ብዝሀነትን ሳይሆን Majesticaዊነትን ለማመልከት ነው” ይላሉ።
- 📖 ዘፍ 1:26
- 📖 ዘፍ 3:22
- 📖 ዘፍ 11:7
- 📖 ኢሳ 6:8
- 📖 ዕብ 1 (መዝ 45፣ 101ን ይጠቅሳል)
2) አዲስ ኪዳን
- 📖 ማቴ 3:16-17
- 📖 ማቴ 28:19-20
- በሶስትነት አንድነት!
- 📖 1ቆሮ 12:4-6
- እግዚአብሔር አብን አባት
- እግዚአብሔር ወልድ ጌታ
- እግዚአብሔር መንፈስ መንፈስ ቅዱስ
- 📖 ኤፌ 4:4-6
- 📖 ይሁዳ 1:20-21
🖊 ሁሉን በፈጠረ፣ ከሁሉ በላይ በሆነ፣ እናውቀውና እናመልከው ዘንድ ራሱን በገለጠ፣ ደግሞም በባሕርይ አንድ፣ በአካል ሦስት፦ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆኖ ለዘላለም በሚኖር አንድ አምላክ እናምናለን።