የእግዚአብሔር ባሕርያት ክፍል 2 (Attributes of God Part 2)
እግዚአብሔርን የምናውቅበት አንዱ መንገድ ባህርያቱን ማወቅ ነው። ባሕርያቱን ባወቅን ቁጥር እግዚአብሔርን እናውቀዋለን።
4) ሁሉን ቻይነት (OMNIPOTENT)
- እግዚአብሔር የማይገመት ኃይል አለው ። ሁሉን የማድረግ ሀይል አለው፣ ስራውን እንጂ የምናየው የማይሠፈር ሀይል ያለው ነው።
- የእግዚአብሔር ኃይል ይሔን ያህላል አይባልም። የኃይል መመዘኛ አይችለውም።
📖 ዘፍ 1:1 – ብቻውን ሁሉን ይችላል። (በፍጥረቱ ተገልጧል)
📖 ኤፌ 1:19 – የማይገመት ኃይሉ ተገልጧል። ከሁሉ በላይ ታላቅ የሆነው ኃይሉ የታየበት መንገድ ኢየሱስን ከሞት ሲያስነሳውና በቀኙ ሲያስቀምጠው ነው። - የእግዚአብሔር ሁሉንቻይነት ስናነሳ ከባሕሪው ጋር ነው። ከባሕሪው ጋር የማይሔድ ነገር የማያደርገው አቅም ስለሌለው/ ኃይል ስላጠረው ሳይሆን ባሕሪው ስላልሆነ ነው።
📖 ዘፍ 17:1 –
📖 ዘፍ 18:14
📖 ሉቃ 1:37 - እንደ ሀይሉ መጠን የሚሠራ አምላክ እናመልካለን።
📖 ኤፌ 3:20-21 - ሁሉን ቻይ ነው ስንል በልምድና በጊዜ ያገኘው ነገር አይደለም። እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ነው ስንል መረጃ ሰብስቦ ወይም ተምሮ አይደለም፤ በባህሪው እሱ እንደዚሁ ነው። አምላክን አምላክ ያደረገው ይሔ ነው።
- ቤተክርስቲያን የቴክኖሎጂ ጠላት አይደለም፤ ነገር ግን የአምላክን ባህሪ ለሰው የማቅረብ አይነት፣ አምላክን የመፍጠር አይነት፤ በእግዚአብሔር እንዳንደነቅ የሚያደርጉ ባህሪያት የሚገለጡባቸው ነገሮች ግን በዚህ ዘመን አለ።
- AI ሰው አጠራቅሞበት ነው process የሚያደርገው ግን ህሊና የለውም። የእግዚአብሔርን በሁሉ ቦታ በአንድ ጊዜ መገኘት ለማጥፋት እያደገ ያለ ነገር አለ። ሁሉን አዋቂ መሳይ ነገር እየመጣ ነው። እንንቃ!
- ከእግዚአብሔር ይልቅ በሱ መደነቅ እንድናበዛ ያደርገናል።
- እንደዚህ አይነት ቴክኖሎጂ እንደመሣሪያ መጠቀም ጥሩ ነው፤ ነገር ግን አካሔዳቸውን መመዘን ጥሩ ነው። ምክንያቱም የያዛቸውን ነው የሚመስሉት።
- ስለ ሁሉም ነገር በነሱ ላይ የሚደገፍ እንዳትሆኑ፣ ሁሉን ቻይ መስሎን በሱ ላይ የሚደገፍ እንዳትሆኑ፣ አንዳንድ እውቀታችሁን እንዳትጥሉ፣ ጥገኛ እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ።
- የቴክኖሎጂ አምላኪነት ልክ ሊኖረው ይገባል፤ ልክ የሌለው እግዚአብሔር ነው።
- መደነቂያ አምላክ መሠል ነገሮች እየመጡ ነው። እውቀት ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ነው።
📍እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር ባለው ግንኙነት የሚገለጡ (የሚጋሩ/የሚያሸጋግሩ)
ሙሉ ለሙሉ የሚጋራቸው ባይሆኑም በተወሰነ ደረጃ ግን ይጋራቸዋል።
1) ቅድስና (HOLINESS)
እግዚአብሔር ቅዱስ ነው!
ቅዱስ ማለት የተለየ፣ ተመሳሳይ የሌለ፣ የራቀ ማለት ነው።
የእግዚአብሔርን ቅድስና ስናነሳ ከሁለት አቅጣጫ መመልከት አንችላለን
A) የእግዚአብሔር ልዩትነት (UNIQUENESS)
የተለየ ነው፣ አይነጻጸርም፣ የሚመስለው የሌለ፣ ያልተነካካ፣ ከፍ ያለ ነው።
📖 1ሳሙ 2:2
ቅድስና ከማንም አይጀምርም፣ ከፍጥረት አይጀምርም፤ ብቻውን ነው።
📖 ኢሳ 6:1-3
📖 1ጢሞ 6:16
B) ፍጹም የሆነ ንጽሕና (PERFECT PURITY)
የእግዚአብሔርን ፍጹም የሆነ ንጽሕና አመላካች ነው።
ከክፋት፣ ከኃጢአት የጸዳ፣ ንጹህ የሆነ አምላክ ነው።
📖 ኢዮ 34:10
📖 እንባቆም 1:13
ጠማምነት፣ ክፉ፣ የረከሰ ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ የለም።
ይሔ የእግዚአብሔር የሚጋራ ባህርይ ነው። የሚጋራው ብቻ ሳይሆን የሚጠበቅብን ባህሪ ነው።
ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖሩ ሁሉ የሚጠበቅባቸው ባህሪ ይሔ ነው።
📖 ዘሌ 11:44-45
📖 1ጴጥ 1:15-16
የእግዚአብሔር የቅድስና Standard የምንካፈለው ነው።
ቅድስና ዘመን የማይሽር ትምህርት ነው።
እግዚአብሔር ከሕዝቡ የሚፈልገው የቅድስና concept የብሉይ ኪዳን አይደለም።
ትዕዛዝ ተጭኖብን ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ከመሆናችን የተነሳ የተጋራነው ባሕሪ ነው።
📖 2ቆሮ 6:14
በእግዚአብሔር ፍርሀት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ስጋንና ከሚያረክስ ነገር ራስን በመጠበቅ መቀደስ ይቻላል።
ጨለማን ከብርሃን፣ የረከሰን ከተቀደሰ ጋር አናጋጥም። በእግዚአብሔር ፍርሀት ስጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር እየጠበቅን ቅድስናን ፍጹም እናድርግ።
ቅድስናን ማመቻቸት የመቆም ምልክት ነው።
2) ጽድቅና ፍትህ (RIGHTEOUSNESS)
እግዚአብሔር በቀና ይፈርዳል፣ በትክከል ይዳኛል፣ በሕግ አይገዛም ሕግ ግን አክባሪ ነው፣ በሕጉ ነው የሚሠራው፣ ለሠው ፊት አያደላም፣ ጻድቅ አምላክ ነው፣ መተላለፍን ይቀጣል፣ መታዘዝን ይባረካል።
የሰው ፊት ወይም መደለያ ምንም አያደርገውም። የእውነት አምላክ ነው፣ የጽድቅ አምላክ ነው፣ በቅንነት፤ በትክክል፤ በእውነት፤ በጽድቅ ይፈርዳል፤ ይዳኛል።
📖 መዝ 89:14 – (የዙፋንህ መሠረት ጽድቅና ፍርድ ነው)
📖 ዘጸ 34:6-7 – (እግዚአብሔር ሩሕሩህና ቸር አምላክ…በደለኛውን ግን ሳይቀጣ ዝም ብሎ አይተውም)
አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ልክ አይመስለንም፣ ኃጢአተኛን እየሸለመ ይመስለናል፣ ፍርድ የተዛባ ይመስላል፣ እግዚአብሔር ዝም ያለ ይመስላል። የእግዚአብሔር ዝምታ ባህሪውን ያመቻቸ አይደለም። ግን እግዚአብሔር በጽድቅ መፍረዱ አይቀርም።
📖 መዝ 73:17-20
📖 ሐዋ 17:31
ይሔም ከፍጥረት ጋር የሚጋራው ባህሪው ነው። ጻድቅ ፈራጆች እንድንሆን ይፈልጋል፣ ፍርድ ሲጣመም ዝም እንድንል አይፈልግም፣ ፍትህ ሲጓደል እግዚአብሔር ያዝናል።
📖 አሞጽ 3:12
3) ፍቅር (LOVE)
እግዚአብሔር ፍቅእ ነው። ራሱን ለሌሎች በጎነት አሳልፎ የሚሠጥ አምላክ ነው።
የእግዚአብሔር ፍቅር እከከኝ ልከክልህ አይደለም፤ አጋፔ ፍቅር ነው፣ ሳይቀበል የሚሠጥ ነው፣ ያለቅድመ ሁኔታ የሚወድ ነው፣ ለሌሎች የሚኖር ነው።
📖 ዮሐ 3:16
ፍቅሩ ራሱን ሰጪ ነው። በመስጠት የተረጋገጠ እግዚአብሔር ነው። ምላሽ ጠባቂ ሳይሆን እንዲሁ የሚወድ ነው።
የእግዚአብሔር ፍቅርየተገለጠ ነው። ለሀጥአንና ለጻድቅ እኩል ጸሐይን ያወጣል።
የሚያኖረን የእግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ ልግስናው ከፍቅር የመነጨ ነው፣ ዝሞ ብሎ ይወዳል፤ ዝም ብሎ ይሠጣል።
📖 ዘዳ 7:7-8
📖 ዮሐ 17
📍ማጠቃለያ
🖊 የእግዚአብሔር ፍትህ እና የእግዚአብሔር ፍቅር እንዴት አንድ ላይ ይሔዳል?
ፍቅር ሁሉን መተው አይደለም። ፍቅር ይገስጻል። ፍቅር የፍትህ አካል ነው።
የምንወደውን እንገስጻለን፣ የምንወደው ላይ ፍትህን እናረጋግጣለን።
እግዚአብሔር ይወደናል ስንል ምንም አያደርገንም ማለት አይደለም። ይገስጸናል ሊመልሰን ይቀጣናል፣ ስለሚወደን ይቀጣናል።
ተግሳጽ ለእግዚአብሔር ልጆች የፍቅሩ መገለጫ ነው።
እግዚአብሔር ቅዱስ ነው፤ ቅድስናውን ያጓደለውን ነገር ይቀጣል። እግዚአብሔር ደግሞ የፍቅር አምላክ ነው፤ በነጻ በመስጠት ሰዎችን ያቅፋል።